በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጠመቅ ይኖርብኝ ይሆን?

መጠመቅ ይኖርብኝ ይሆን?

ምዕራፍ 37

መጠመቅ ይኖርብኝ ይሆን?

የሚከተሉት ዓረፍተ ነገሮች እውነት ናቸው ወይስ ሐሰት?

ጥምቀት ክርስቲያኖች ሊያሟሉት የሚገባ ብቃት ነው።

□ እውነት

□ ሐሰት

የጥምቀት ዋነኛ ዓላማ ኃጢአት እንዳትሠራ ጥበቃ ማድረግ ነው።

□ እውነት

□ ሐሰት

ጥምቀት መዳን እንድታገኝ መንገድ ይከፍትልሃል።

□ እውነት

□ ሐሰት

ካልተጠመቅህ ለምትፈጽማቸው ድርጊቶች በአምላክ ፊት ተጠያቂ አትሆንም።

□ እውነት

□ ሐሰት

ጓደኞችህ ከተጠመቁ አንተም ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ ማለት ነው።

□ እውነት

□ ሐሰት

አምላክ ያወጣቸውን መመሪያዎች የምትከተል ከሆነ፣ ከአምላክ ጋር ወዳጅነት ከመሠረትክ እንዲሁም ስለ እምነትህ ለሌሎች የምትናገር ከሆነ ስለ መጠመቅ ማሰብህ የተገባ ነው። ይሁንና ይህን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆንህን እንዴት እርግጠኛ መሆን ትችላለህ? ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት እውነት ወይም ሐሰት ብለህ እንድትመልስ ከላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች እስቲ እንመርምር።

ጥምቀት ክርስቲያኖች ሊያሟሉት የሚገባ ብቃት ነው።

እውነት። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እንዲጠመቁ አዟል። (ማቴዎስ 28:19, 20) ኢየሱስ ራሱ ተጠምቋል። አንተም የክርስቶስ ተከታይ ለመሆን መጠመቅ ይኖርብሃል፤ እርግጥ ይህን ውሳኔ ለማድረግ ብስለቱም ሆነ ልባዊ ፍላጎቱ ሊኖርህ ይገባል።

የጥምቀት ዋነኛ ዓላማ ኃጢአት እንዳትሠራ ጥበቃ ማድረግ ነው።

ሐሰት። ጥምቀት ራስህን ለይሖዋ መወሰንህን በሕዝብ ፊት የምታሳይበት እርምጃ ነው። ራስን መወሰን፣ ግዴታ ውስጥ ስለገባህ ብቻ ልብህ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ከማድረግ እንድትቆጠብ የሚያግድ ከአምላክ ጋር የሚደረግ ውል አይደለም። ከዚህ በተቃራኒ ራስህን ለይሖዋ የምትወስነው እሱ ባወጣቸው መሥፈርቶች መሠረት ለመኖር ስለምትፈልግ ነው።

ጥምቀት መዳን እንድታገኝ መንገድ ይከፍትልሃል።

እውነት። ጥምቀት መዳን ለማግኘት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (1 ጴጥሮስ 3:21) መጠመቅ ሲባል ግን አደጋ ቢደርስብህ ሊረዳህ የሚችል የመድን ዋስትና መግዛት ማለት አይደለም። የምትጠመቀው ይሖዋን ስለምትወደውና በሙሉ ልብህ ለዘላለም ልታገለግለው ስለምትፈልግ ነው።​—ማርቆስ 12:29, 30

ካልተጠመቅህ ለምትፈጽማቸው ድርጊቶች በአምላክ ፊት ተጠያቂ አትሆንም።

ሐሰት። ያዕቆብ 4:17 እንደሚገልጸው አንድ ሰው ተጠመቀም አልተጠመቀ “ትክክል የሆነውን ነገር እንዴት ማድረግ እንዳለበት ቢያውቅና ሳያደርገው ቢቀር ኃጢአት ይሆንበታል።” ስለዚህ ትክክል የሆነውን ነገር የምታውቅና በሕይወትህ ውስጥ የታሰበበት ውሳኔ ለማድረግ ብስለቱ ካለህ ጥምቀትን በተመለከተ ከወላጆችህ ወይም ከአንድ የጎለመሰ ክርስቲያን ጋር መወያየት ያስፈልግሃል። እንዲህ ማድረግህ ለመጠመቅ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብህ ለማወቅ ይረዳሃል።

ጓደኞችህ ከተጠመቁ አንተም ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ ማለት ነው።

ሐሰት። ለመጠመቅ የምትወስነው በራስህ ፍላጎት ተነሳስተህ ሊሆን ይገባል። (መዝሙር 110:3) መጠመቅ የሚገባህ ከይሖዋ ምሥክሮች አንዱ ለመሆን የሚያስፈልገውን ብቃት በሚገባ ከተገነዘብክና ይህን ኃላፊነት ለመሸከም ዝግጁ መሆንህን እርግጠኛ ከሆንክ ብቻ ነው።​—መክብብ 5:4, 5

ሕይወትህን የሚለውጥ እርምጃ

ጥምቀት ሕይወትህን የሚለውጥ እርምጃ ሲሆን ብዙ በረከቶችንም ያመጣልሃል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምቀት ከባድ ኃላፊነት ያስከትላል፤ ለይሖዋ ራስህን ስትወስን ከገባኸው ቃል ጋር ተስማምተህ መኖር ይጠበቅብሃል።

ራስህን ለመወሰን ዝግጁ ነህ? ከሆነ ደስ ሊልህ ይገባል። ከሁሉ የላቀ መብት ይጠብቅሃል፤ ይኸውም ይሖዋን በሙሉ ልብህ ለማገልገልና ራስህን የወሰንከው ከልብህ እንደሆነ በሚያሳይ መንገድ ሕይወትህን ለመምራት የሚያስችል አጋጣሚ ይከፈትልሃል።​—ማቴዎስ 22:36, 37

በሚቀጥለው ምዕራፍ

ሕይወትህን በተሻለ መንገድ እንድትጠቀምበት የሚያስችሉህን ግቦች እንዴት ማውጣት እንደምትችል እንመለከታለን።

ቁልፍ ጥቅስ

“ሰውነታችሁን ሕያው፣ ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት አድርጋችሁ [አቅርቡ]፤ . . . ይህም የማሰብ ችሎታችሁን ተጠቅማችሁ የምታቀርቡት ቅዱስ አገልግሎት ነው።”​—ሮም 12:1

ጠቃሚ ምክር

መንፈሳዊ እድገት እንድታደርግ ሊረዳህ የሚችል ሰው በጉባኤ ውስጥ ለማግኘት ጥረት አድርግ፤ ወላጆችህ እንዲህ ዓይነት ሰው ሊጠቁሙህ ይችላሉ።​—የሐዋርያት ሥራ 16:1-3

ይህን ታውቅ ነበር ?

ጥምቀት፣ ለመዳን ብቁ መሆንህን የሚያሳየው “ምልክት” ዋነኛ ገጽታ ነው።​—ሕዝቅኤል 9:4-6

ላደርጋቸው ያሰብኳቸው ነገሮች

ለጥምቀት መብቃት እንድችል የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች በሚገባ ለመረዳት ጥረት አደርጋለሁ፦ ․․․․․

ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ወላጆቼን ልጠይቃቸው የምፈልገው ነገር ․․․․․

ምን ይመስልሃል?

● ጥምቀት በቁም ነገር ሊታሰብበት የሚገባ እርምጃ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

● አንድ ወጣት ለጥምቀት ዝግጁ ሳይሆን ይህን እርምጃ እንዲወስድ የሚያነሳሳው ምን ሊሆን ይችላል?

● አንድ ወጣት ራሱን ለአምላክ ከመወሰንና ከመጠመቅ ወደኋላ እንዲል ሊያደርጉት የማይገቡት ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው?

[በገጽ 306 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

እንደተጠመቅሁ ማሰቤ ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው ውሳኔዎችን እንዳደርግና መጥፎ ውጤት የሚያስከትሉ ጎዳናዎችን ከመከተል እንድቆጠብ ረድቶኛል።”​—ሆሊ

[በገጽ 307 ላይ የሚገኝ ሣጥን/​ሥዕል]

ከጥምቀት ጋር በተያያዘ ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

ጥምቀት ምን ያመለክታል? ውኃ ውስጥ መጥለቅህና ከዚያም መውጣትህ ለራስህ ጥቅም ብቻ በማሰብ ትከተል ለነበረው የሕይወት ጎዳና መሞትህንና የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ ሕያው መሆንህን ያመለክታል።

ራስህን ለይሖዋ መወሰን ሲባል ምን ማለት ነው? ራስህን በመካድ የይሖዋ ንብረት መሆንህንና የአምላክን ፈቃድ ከማንኛውም ነገር ለማስቀደም ቃል መግባትህን ያመለክታል። (ማቴዎስ 16:24) በመሆኑም ከመጠመቅህ ቀደም ብለህ ራስህን ለይሖዋ መወሰንህን በጸሎት መግለጽህ የተገባ ነው።

ከመጠመቅህ በፊት ምን ማድረግ ይጠበቅብሃል? ከአምላክ ቃል ጋር በሚስማማ መንገድ መኖር እንዲሁም ስለ እምነትህ ለሌሎች መናገር ይኖርብሃል። በተጨማሪም በመጸለይና የአምላክን ቃል በማጥናት ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት መመሥረት ይኖርብሃል። ይሖዋን ማገልገል ያለብህ ሌሎች ስለገፋፉህ ሳይሆን አንተ ራስህ ስለፈለግህ ሊሆን ይገባል።

መጠመቅ የሚገባህ በስንት ዓመትህ ነው? ወሳኙ ጉዳይ ዕድሜ አይደለም። ያም ሆኖ ራስህን መወሰንህ ምን ትርጉም እንዳለው ለመረዳት የሚያስችልህ ዕድሜና ብስለት ሊኖርህ ይገባል።

አንተ ለመጠመቅ ብትፈልግም ወላጆችህ ልትቆይ እንደሚገባ የሚሰማቸው ቢሆንስ? እንዲህ የሚሉህ ክርስቲያን መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ የበለጠ ተሞክሮ እንድታገኝ ስለፈለጉ ሊሆን ይችላል። ምክራቸውን ስማ፤ እንዲሁም ይህን አጋጣሚ ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማጠናከር ተጠቀምበት።​—1 ሳሙኤል 2:26

[በገጽ 308 እና 309 ላይ ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የመልመጃ ሣጥን

ለመጠመቅ እያሰብክ ነው?

ለጥምቀት የሚያበቃ እድገት እያደረግህ መሆንህን ለማወቅ ከታች በቀረቡት ጥያቄዎች በመጠቀም ራስህን ገምግም። መልስህን ከመጻፍህ በፊት ጥቅሶቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥተህ አንብብ።

ይሖዋ መታመኛህ መሆኑን አሁን እያሳየህ ያለኸው በየትኞቹ መንገዶች ነው?​መዝሙር 71:5 ․․․․․

ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር ለመለየት የማስተዋል ችሎታህን እንዳሠለጠንከው በሕይወትህ ውስጥ ያሳየኸው እንዴት ነው?​ዕብራውያን 5:14 ․․․․․

ምን ያህል አዘውትረህ ትጸልያለህ? ․․․․․

ስለ አንድ ጉዳይ ስትጸልይ ሐሳብህን በግልጽ ትናገራለህ ወይስ እንዲያው በደፈናው ታስቀምጠዋለህ? ጸሎትህ ለይሖዋ ስላለህ ፍቅር ምን ያሳያል?​መዝሙር 17:6 ․․․․․

ከጸሎት ጋር በተያያዘ ልታወጣው የምትፈልገውን ማንኛውንም ግብ ከዚህ በታች ጻፍ። ․․․․․

መጽሐፍ ቅዱስን ምን ያህል አዘውትረህ ታጠናለህ?​ኢያሱ 1:8 ․․․․․

በግል ጥናትህ ወቅት የትኞቹን ነገሮች ታጠናለህ? ․․․․․

ከግል ጥናት ጋር በተያያዘ ልታወጣው የምትፈልገውን ማንኛውንም ግብ ከዚህ በታች ጻፍ። ․․․․․

ትርጉም ያለው አገልግሎት እያከናወንክ ነው? (ለምሳሌ፦ መሠረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ለሰዎች ማብራራት ትችላለህ? ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ተመልሰህ ትጠይቃለህ? የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማግኘት ጥረት ታደርጋለህ?)

□ አዎ □ አይ

ወላጆችህ በአገልግሎት ባይካፈሉም እንኳ አንተ እንዲህ ታደርጋለህ?​የሐዋርያት ሥራ 5:42

□ አዎ □ አይ

ከአገልግሎትህ ጋር በተያያዘ ልታወጣው የምትፈልገውን ማንኛውንም ግብ ከዚህ በታች ጻፍ።​2 ጢሞቴዎስ 2:15 ․․․․․

በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ አዘውትረህ ትገኛለህ? ወይስ አልፎ አልፎ የመቅረት ልማድ አለህ?​ዕብራውያን 10:25 ․․․․․

በስብሰባዎች ላይ በየትኞቹ መንገዶች ተሳትፎ ታደርጋለህ? ․․․․․

ወላጆችህ ስብሰባ መሄድ ባይችሉም እንኳ (የሚፈቅዱልህ ከሆነ) አንተ ትሄዳለህ?

□ አዎ □ አይ

የአምላክን ፈቃድ ማድረግ እንደሚያስደስትህ ከልብህ መናገር ትችላለህ? ​መዝሙር 40:8

□ አዎ □ አይ

የእኩዮችህን ተጽዕኖ የተቋቋምክባቸውን አንዳንድ አጋጣሚዎች መጥቀስ ትችላለህ?​ሮም 12:2 ․․․․․

ለይሖዋ ያለህ ፍቅር ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ምን ለማድረግ አስበሃል?​ይሁዳ 20, 21 ․․․․․

ወላጆችህና ጓደኞችህ ይሖዋን ማገልገላቸውን ቢያቆሙም እንኳ አንተ ታገለግለዋለህ?​ማቴዎስ 10:36, 37

□ አዎ □ አይ

[በገጽ 310 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ልክ እንደ ጋብቻ ጥምቀትም ሕይወትህን የሚለውጥ እርምጃ በመሆኑ አቅልለህ ልትመለከተው አይገባም