በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ወላጆችህ

ወላጆችህ

ክፍል 6

ወላጆችህ

ወላጆች በሕይወታቸው ውስጥ ብዙ ተሞክሮ አካብተዋል። በጉርምስና ወቅት ከሚከሰቱት አካላዊና ስሜታዊ ለውጦች ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙትን ግራ የሚያጋቡ ሁኔታዎች በሕይወታቸው ውስጥ አስተናግደዋል። ከዚህ አንጻር ወላጆችህ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት እንድትወጣ አንተን ለመርዳት ከማንም የተሻለ ብቃት ሊኖራቸው ይገባል ማለት ይቻላል። ይሁን እንጂ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው አንዳንድ ጊዜ ወላጆችህ እርዳታ ከመስጠት ይልቅ እነሱ ራሳቸው ተጨማሪ ችግር እንደሚፈጥሩ ይሰማህ ይሆናል። ለምሳሌ ከታች ከተዘረዘሩት ተፈታታኝ ሁኔታዎች አንዱ በአንተ ላይ ደርሶ ሊሆን ይችላል፦

ወላጆችህ ሁልጊዜ ይነቅፉሃል።

አባትህ ወይም እናትህ የዕፅ አሊያም የአልኮል ሱሰኞች ናቸው።

ወላጆችህ ሁልጊዜ ይጨቃጨቃሉ።

ወላጆችህ ተለያይተዋል።

ከ21 እስከ 25 ያሉት ምዕራፎች እነዚህንና ሌሎች ችግሮችን መቋቋም እንድትችል ይረዱሃል።

[በገጽ 172 እና 173 ላይ የሚገኝ ባለሙሉ ገጽ ሥዕል]