በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሕይወቴ ደስተኛ አይደለሁም—ከሃይማኖት፣ ከአምላክ ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ እርዳታ ላገኝ እችላለሁ?

በሕይወቴ ደስተኛ አይደለሁም—ከሃይማኖት፣ ከአምላክ ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ እርዳታ ላገኝ እችላለሁ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 አዎ፣ የጥበብ ጎተራ የሆነውና በጥንት ዘመን የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወት ውስጥ ለሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፤ እንዲሁም ደስተኛ እንድትሆንና የተረጋጋ ሕይወት እንድትመራ ይረዳሃል። መጽሐፍ ቅዱስ መልስ ከሚሰጣቸው ጥያቄዎች መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፦

  1.   ፈጣሪ አለ? መጽሐፍ ቅዱስ ‘ሁሉንም ነገሮች የፈጠረው’ አምላክ እንደሆነ ይናገራል። (ራእይ 4:11) አምላክ ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን ደስተኛና አርኪ ሕይወት ለመምራት ምን እንደሚያስፈልገን ያውቃል።

  2.   አምላክ ስለ እኔ ያስባል? መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ከሰው ልጆች የራቀ እንደሆነ አይገልጽም፤ ከዚህ ይልቅ “እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ . . . አይደለም” ይላል። (የሐዋርያት ሥራ 17:27) በሕይወትህ ውስጥ የሚያጋጥሙህን ነገሮች ትኩረት ሰጥቶ ይከታተላል፤ እንዲሁም ስኬታማ እንድትሆን ይፈልጋል።​—ኢሳይያስ 48:17, 18፤ 1 ጴጥሮስ 5:7

  3.   አምላክን ማወቅ ደስተኛ እንድሆን የሚረዳኝ እንዴት ነው? አምላክ ሲፈጥረን መንፈሳዊ ፍላጎት እንዲኖረን አድርጎ ነው፤ ይህም ሲባል የሕይወትን ትርጉም የማወቅ ተፈጥሯዊ ጉጉት አለን ማለት ነው። (ማቴዎስ 5:3) መንፈሳዊ ፍላጎታችን ፈጣሪያችንን ማወቅንና ከእሱ ጋር ወዳጅነት መመሥረትን ይጨምራል። አምላክ እሱን ለማወቅ የምናደርገውን ጥረት ይባርክልናል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል” ይላል።​—ያዕቆብ 4:8

 በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከአምላክ ጋር ወዳጅነት በመመሥረታቸው ሕይወታቸው እንደተሻሻለና ደስተኛ ሕይወት መምራት እንደጀመሩ ይሰማቸዋል። አምላክን ማወቅ ከችግር ነፃ የሆነ ሕይወት እንድትመራ ባያደርግም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ የሚከተሉትን ነገሮች እንድታገኝ ይረዳሃል፦

 በመጽሐፍ ቅዱስ እንመራለን የሚሉ በርካታ ሃይማኖቶች በውስጡ ያለውን ትምህርት አይከተሉም። በአንጻሩ ግን እውነተኛው ሃይማኖት የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት በጥብቅ የሚከተል ሲሆን አምላክን እንድታውቀውም ይረዳሃል።