በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች

በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች

ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቁ ብዙ ሁኔታዎች በየዕለቱ ያጋጥሙናል። በዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ውሳኔ የሚያደርጉት በስሜት ተገፋፍተው አሊያም ብዙሃኑን ተከትለው ነው። (ዘፀ 23:2፤ ምሳሌ 28:26) በይሖዋ የሚታመኑ ሰዎች ግን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ ተመሥርተው ውሳኔ በማድረግ ‘እሱን ግምት ውስጥ ያስገባሉ።’—ምሳሌ 3:5, 6

የሚከተሉት ጥቅሶች ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የሚረዱህ በየትኞቹ ሁኔታዎች ውስጥ ነው? ለእያንዳንዱ ጥቅስ አንድ ምሳሌ ስጥ።

የእምነት የለሾችን ሳይሆን የእምነት ሰዎችን ምሳሌ ተከተሉ—ፈርዖንን ሳይሆን ሙሴን የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

ወንድማችን የአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪክ ምሳሌ ጥሩ ውሳኔ እንዲያደርግ የረዳው እንዴት ነው?