በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የውይይት ናሙናዎች
የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ (ከመጋቢት 11–ሚያዝያ 4)
“በአንድ ልዩ በዓል ላይ እንዲገኙ ብንጋብዝዎት ደስ ይለናል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን በዓል ያከብራሉ። ይህ በዓል የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ ነው።” የታተመውን መጋበዣ ስጠው ወይም የኤሌክትሮኒክ ቅጂውን ላክለት። “ይህ የመጋበዣ ወረቀት ስብሰባው በአካባቢያችን የሚደረግበትን ቦታና ሰዓት ይገልጻል። ከበዓሉ በፊት ባለው ሳምንት ደግሞ ልዩ ንግግር ይኖረናል፤ ይህን ንግግርም ቢያዳምጡ ደስ ይለናል።”
ፍላጎት ካሳየ፦ የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት [አሊያም በጽሑፍ መልእክት ወይም በኢሜይል ላክ]።
ለቀጣዩ ጊዜ፦ ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?
መመሥከር (ከመጋቢት 1-10፣ ከሚያዝያ 5-30)
ተመላልሶ መጠየቅ
ጥያቄ፦ ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው?
ጥቅስ፦ ማቴ 20:28
ለቀጣዩ ጊዜ፦ ኢየሱስ ለከፈለልን ቤዛዊ መሥዋዕት አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?