በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 90

እርስ በርስ እንበረታታ

እርስ በርስ እንበረታታ

(ዕብራውያን 10:24, 25)

  1. 1. እርስ በርስ ስንበረታታ፣

    ታማኝ ሆነን ለማገልገል፣

    ዝምድናችን ይጠናከራል፤

    ሰላም፣ ኅብረት ይኖረናል።

    በኛ መካከል ያለው ፍቅር፣

    ድፍረት፣ ብርታት ይሰጠናል።

    ጉባኤ ጥበቃ ያስገኛል፤

    በዚያ መሆን ያረጋጋል።

  2. 2. በጊዜው የተነገረ ቃል፣

    እንዴት ’ሚያጽናና ይሆናል!

    እንዲህ ዓይነት ቃል እንሰማለን፣

    ከታማኝ ወዳጆቻችን።

    ደስ ይለናል አብረን ስንሠራ፣

    ስላለን አንድ ዓይነት ተስፋ።

    እርስ በርስ እንበረታታ፤

    ሁሉም ሸክሙን እንዲወጣ።

  3. 3. በእምነት ዓይን ስለሚታየን

    መቅረቡ የይሖዋ ቀን፣

    ከሕይወት መንገድ እንዳንወጣ

    መሰብሰብ አለብን አብረን።

    ዘላለም ’ናገለግላለን፣

    ካምላክ ሕዝቦች ጋር አንድ ሆነን።

    ንጹሕ አቋማችን እንዳይጎድፍ

    እርስ በርስ እንደጋገፍ።

(በተጨማሪም ሉቃስ 22:32⁠ን፣ ሥራ 14:21, 22⁠ን፣ ገላ. 6:2⁠ን እና 1 ተሰ. 5:14⁠ን ተመልከት።)