በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 91

በፍቅር ተነሳስተን ያከናወንነው ሥራ

በፍቅር ተነሳስተን ያከናወንነው ሥራ

(መዝሙር 127:1)

  1. 1. አበቃኸን ለዚህ ቀን፤

    ልዑሉ አምላክ ተመስገን።

    ያሳየኸን ሞገስ፣ ክብርህም፣

    ቃል አይገልጸውም።

    አይተህ ድካማችንን፣

    ባርከኸዋል ሥራችንን።

    ላንተ የሠራነው ይህ ሕንፃ፣

    ያሳያል ይህን።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ሆይ፣ ላንተ ቤት መሥራት፣

    ነው ለኛ እጅግ ታላቅ መብት።

    ዕድሜያችንን በሙሉ አንተን እናምልክህ፤

    በሥራችን እናክብርህ።

  2. 2. ሁላችን ደስ ብሎናል፤

    ዝምድናችንም ጠንክሯል።

    ይህ ትዝታ ከቶ አይጠፋም፤

    እስከ ዘላለም!

    በአንድነት ለመሥራት

    ሆኖናል መንፈስህ ረዳት።

    ስምህን ከፍ ከፍ አ’ርገናል፤

    ተደስተናል።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ሆይ፣ ላንተ ቤት መሥራት፣

    ነው ለኛ እጅግ ታላቅ መብት።

    ዕድሜያችንን በሙሉ አንተን እናምልክህ፤

    በሥራችን እናክብርህ።

(በተጨማሪም መዝ. 116:1⁠፤ 147:1⁠ን እና ሮም 15:6⁠ን ተመልከት።)