በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 89

ስማ፣ ታዘዝ፤ ትባረካለህ

ስማ፣ ታዘዝ፤ ትባረካለህ

(ሉቃስ 11:28)

  1. 1. ክርስቶስን ሰምተን ስንታዘዘው፣

    ትምህርቶቹ ብርሃን ይሆኑናል።

    መስማትና ማወቅ ያስደስተናል፤

    መታዘዝ ግን በረከት ያስገኛል።

    (አዝማች)

    አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣

    ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

    ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣

    ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

  2. 2. በዓለት ላይ የተመሠረተ ቤት፣

    ለሰው ከለላ ’ንደሚሆንለት፣

    የኢየሱስን ትምህርቶች መከተል፣

    ሕይወታችንን ይጠብቀዋል።

    (አዝማች)

    አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣

    ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

    ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣

    ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

  3. 3. በጅረቶች ዳር የተተከለ ዛፍ፣

    በየወቅቱ ፍሬ እንደሚሰጥ፣

    እንደ ልጆቹ አምላክን ብንሰማው፣

    ይሰጠናል የዘላለም ሕይወት።

    (አዝማች)

    አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣

    ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

    ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣

    ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

(በተጨማሪም ዘዳ. 28:2⁠ን፣ መዝ. 1:3⁠ን፣ ምሳሌ 10:22⁠ን፣ ማቴ. 7:24-27⁠ን እና ሉቃስ 6:47-49⁠ን ተመልከት።)