በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ገንዘብ

ገንዘብ

ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው?

“የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነው።”—1 ጢሞቴዎስ 6:10

አንዳንዶች ምን ይላሉ?

ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

‘ለብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች’ የሚዳርገው ገንዘብ ራሱ ሳይሆን “የገንዘብ ፍቅር” ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰው ባለጸጋ የነበረው ንጉሥ ሰለሞን ገንዘብ በሚወዱ ሰዎች ላይ ብዙውን ጊዜ የሚደርሱትን ሦስት ጎጂ ነገሮች ዘርዝሯል። ጭንቀት፦ “የሀብታም ሰው ብልጽግና ግን እንቅልፍ ይነሣዋል።” (መክብብ 5:12) እርካታ ማጣት፦ “ገንዘብን የሚወድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድ፣ በትርፉ አይረካም።” (መክብብ 5:10) ሕግ ለመጣስ መፈተን፦ “ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ንጽሕናውን ማጉደፉ አይቀርም።”—ምሳሌ 28:20 NW

 ገንዘብ ለምን ዓላማ ያገለግላል?

“ገንዘብ ጥላ ከለላ . . . ነው።”—መክብብ 7:12

አንዳንዶች ምን ይላሉ?

ገንዘብ ካለህ ከስጋት ነፃ የሆነ ኑሮ ትኖራለህ፤ እንዲሁም ደስተኛ ትሆናለህ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ገንዘብ ደስታና ከስጋት ነፃ የሆነ ሕይወት ያስገኛል የሚለው የተሳሳተ እምነት “ሀብት ያለው የማታለል ኃይል” አንድ ክፍል ነው። (ማርቆስ 4:19) ያም ሆኖ “ገንዘብ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያሟላል።” (መክብብ 10:19 NW) ለምሳሌ፣ ገንዘብ ለሕይወት የሚያስፈልጉ እንደ ምግብና መድኃኒት ያሉ ነገሮችን ሊገዛ ይችላል።—2 ተሰሎንቄ 3:12

በተጨማሪም ገንዘብ ቤተሰብህን ለማስተዳደር ይረዳሃል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “አንድ ሰው የራሱ ለሆኑት በተለይ ደግሞ ለቤተሰቡ አባላት የሚያስፈልጋቸውን ነገር የማያቀርብ ከሆነ እምነትን የካደ . . . ነው።”—1 ጢሞቴዎስ 5:8

ገንዘብን በጥበብ ልትጠቀምበት የምትችለው እንዴት ነው?

‘በመጀመሪያ ተቀምጠህ ወጪህን አስላ።’—ሉቃስ 14:28

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ገንዘብህን አምላክ ደስ በሚሰኝበት መንገድ ተጠቀምበት። (ሉቃስ 16:9) ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ሐቀኛና ኃላፊነት የሚሰማህ ሰው መሆንህ ጥበብ ነው። (ዕብራውያን 13:18) ከአቅም በላይ መኖር ከሚያስከትለው ሸክም ለመዳን አኗኗርህ “ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን።”—ዕብራውያን 13:5

መጽሐፍ ቅዱስ መበደርን ባያወግዝም ‘ተበዳሪ የአበዳሪ ባሪያ ነው’ የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። (ምሳሌ 22:7) ያየኸውን ሁሉ የመግዛት ልማድን አስወግድ፤ ምክንያቱም ‘ችኰላ ወደ ድኽነት ያደርሳል።’ (ምሳሌ 21:5) ከዚህ ይልቅ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ለማዋል እንድትችል ‘እንደ ገቢህ ሁኔታ የተወሰነ መጠን’ ገንዘብ ቆጥብ።—1 ቆሮንቶስ 16:2

መጽሐፍ ቅዱስ “ሰጪዎች” እንድንሆን ያበረታታናል። (ሉቃስ 6:38) አምላክን ለማስደሰት የሚፈልጉ ሰዎች ለጋሶች መሆናቸው የሚጠበቅ ነገር ነው፤ ምክንያቱም አምላክ “በደስታ የሚሰጠውን ሰው [ይወዳል]።” (2 ቆሮንቶስ 9:7) ስለዚህ ‘መልካም ማድረግንና ያለህን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሳ፤ ምክንያቱም አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታል።’—ዕብራውያን 13:16