በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ማስተዋወቂያዎች

እነዚህ አጫጭር ቪዲዮዎች የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ይዘትና ከመጽሐፉ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ይዘዋል። እነዚህ ቪዲዮዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህና ጥናትህ ይበልጥ ጥቅም እንድታገኝ ይረዱሃል።

የዘፍጥረት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ሰው ልጆች አፈጣጠር እንዲሁም መከራና ሞት የመጡት እንዴት እንደሆነ ይናገራል።

የዘፀአት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

አምላክ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ነፃ ያወጣቸውና እሱን እንዲያገለግሉ በብሔር ደረጃ ያደራጃቸው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የዘሌዋውያን መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የዘሌዋውያን መጽሐፍ የአምላክን ቅድስና ይገልጻል፤ እኛም ቅዱስ መሆናችን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል።

የዘኁልቁ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋን መታዘዝና እሱ ሕዝቡን እንዲመሩ የሾማቸውን ሰዎች ማክበር አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ተመልከት።

የዘዳግም መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ሕግ ለሕዝቦቹ ያለውን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የኢያሱ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

እስራኤላውያን አምላክ የሰጣቸውን ምድር የተቆጣጠሩትና የተከፋፈሉት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የመሳፍንት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በተለያዩ ክንውኖች የተሞላው ይህ መጽሐፍ ስያሜውን ያገኘው አምላክ እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው ለመታደግ ከተቀመባቸው ደፋር መሳፍንት ነው።

የሩት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የሩት መጽሐፍ የሚተርከው አንዲት ወጣት መበለት ለአማቷ ስላሳየችው ጥልቅ ፍቅርና ይሖዋ ስለሰጣቸው በረከት ነው።

የ1 ሳሙኤል ማስተዋወቂያ

እስራኤላውያን ከመሳፍንት ዘመን ወደ ነገሥታት ዘመን የተሸጋገሩት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የ2 ሳሙኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ዳዊት ትሑትና ጠንካራ እምነት ያለው ሰው ነበር። እነዚህ ባሕርያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰዎች መካከል በጣም ተወዳጅና በስፋት የሚታወቅ እንዲሆን ያደረጉት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የ1 ነገሥት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

እስራኤል በሰሎሞን አገዛዝ ሥር ታላቅ ክብርና ብልጽግና ነበራት፤ ከዚያ በኋላ ብሔሩ ለሁለት ሲከፈል የተቋቋሙት የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥታት ታሪክ ግን ሁከት የነገሠበት ነው።

የ2 ነገሥት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ክህደት ለሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት እንደ መቅሰፍት ሆኖበታል፤ ያም ቢሆን ይሖዋ እሱን በሙሉ ልብ ያገለገሉትን ጥቂት ሰዎች ባርኳቸዋል።

የ1 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይህ መጽሐፍ፣ ፈሪሃ አምላክ የነበረውን የንጉሥ ዳዊትን የትውልድ ሐረግ መስመር እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ ከተሾመበት እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ያለውን አስገራሚ ታሪክ ይዟል።

የ2 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ለአምላክ ታማኝ የመሆንን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የዕዝራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋ በባቢሎን ምርኮ የነበሩትን ሕዝቦቹ ነፃ ለማውጣትና በኢየሩሳሌም ንጹሑን አምልኮ ለማቋቋም የገባውን ቃል ፈጽሟል።

የነህምያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የነህምያ መጽሐፍ በዛሬው ጊዜ ላሉ እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች በሙሉ የሚሆን ጠቃሚ ትምህርት ይዟል።

የአስቴር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በአስቴር ዘመን የተፈጸሙ አስገራሚ ክንውኖች አምላክ ሕዝቦቹን ከአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የማውጣት ችሎታ እንዳለው ጠንካራ እምነት እንዲያድርብህ ያደርጋል።

የኢዮብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋን የሚወዱ ሁሉ መፈተናቸው አይቀርም። የኢዮብ መጽሐፍ፣ ንጹሕ አቋማችንን መጠበቅና የይሖዋን ሉዓላዊነት መደገፍ እንደምንችል እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል።

የመዝሙር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የመዝሙር መጽሐፍ የይሖዋን ሉዓላዊነት ይደግፋል፤ ይሖዋ የሚወዱትን ሰዎች እንዴት እንደሚረዳና እንደሚያጽናና ይናገራል፤ እንዲሁም በአምላክ መንግሥት አማካኝነት ምድር ገነት እንደምትሆን ይናገራል።

የምሳሌ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የምሳሌ መጽሐፍ ከሥራ ጉዳዮች አንስቶ እስከ ቤተሰብ ሕይወት ድረስ በሁሉም የሕይወታችን ዘርፎች የሚጠቅሙንን መለኮታዊ መመሪያዎች ይዟል።

የመክብብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ንጉሥ ሰለሞን በሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች የትኞቹ እንደሆኑ ይናገራል፤ እንዲሁም እነዚህን ነገሮች ከአምላካዊ ጥበብ ጋር ከሚጻረሩ ነገሮች ጋር ያወዳድራል።

የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ሱላማዊቷ ልጃገረድ ለእረኛው የነበራት የማይከስም ፍቅር ‘የያህ ነበልባል’ ተብሎ ተገልጿል። እንዲህ የተባለው ለምንድን ነው?

የኢሳይያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የኢሳይያስ መጽሐፍ ይሖዋ የገባውን ቃል የሚፈጽምና የሚታደግ አምላክ በመሆኑ ላይ ያለንን እምነት እንድናጠናክር የሚረዱ ትክክለኛ ትንቢቶችን የያዘ መጽሐፍ ነው።

የኤርምያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ኤርምያስ ችግሮች ቢያጋጥሙትም ኃላፊነቱን በታማኝነት ተወጥቷል። እሱ የተወው ምሳሌ በዛሬው ጊዜ ላሉ ክርስቲያኖች የሚጠቅማቸው እንዴት እንደሆነ አስብ።

የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በነቢዩ ኤርምያስ የተጻፈው የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ በኢየሩሳሌም ላይ የደረሰው ጥፋት ያስከተለውን ሐዘንና ንስሐ መግባት የአምላክን ምሕረት የሚያስገኘው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።

የሕዝቅኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ሕዝቅኤል ከአምላክ የተቀበለው ሥራ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳ ኃላፊነቱን በትሕትናና በድፍረት ተወጥቷል።

የዳንኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ዳንኤልና ጓደኞቹ ምንም ዓይነት ሁኔታ ቢያጋጥማቸው ለይሖዋ ታማኝ መሆናቸውን አሳይተዋል። እነሱ የተዉት የታማኝነት ምሳሌም ሆነ በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙት ፍጻሜያቸውን ያገኙ ትንቢቶች በመጨረሻው ዘመን ለምንኖረው ለእኛ ጠቃሚ ናቸው።

የሆሴዕ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የሆሴዕ ትንቢት ይሖዋ ንስሐ ለገቡ ኃጢአተኞች ከሚያሳየው ምሕረትና በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ካለው አምልኮ ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ትምህርት ይዞልናል።

የኢዩኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ኢዩኤል በፍጥነት እየቀረበ ስላለው ‘ስለ ታላቁ የይሖዋ ቀን’ እና ከዚያ ቀን መትረፍ ስለሚቻልበት መንገድ ትንቢት ተናግሯል። ኢዩኤል በትንቢት የተናገረለት ቀን ዛሬ ይበልጥ ወደ ፍጻሜው እየገሰገሰ ነው።

የአሞጽ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋ ትሑት የነበረውን አሞጽን አስፈላጊ የሆነ ሥራ ለማከናወን ተጠቅሞበታል። እኛስ አሞጽ ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?

የአብድዩ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የአብድዩ መጽሐፍ በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ካሉት መጻሕፍት መካከል አጭሩ ነው። ይህ ትንቢት ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ የሚፈነጥቅ ሲሆን የይሖዋ ንግሥና ትክክለኝነት እንደሚረጋገጥ ይናገራል።

የዮናስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ነቢዩ ዮናስ የተሰጠውን ተግሣጽ ተቀብሏል፤ ተልእኮውን ፈጽሟል እንዲሁም ስለ አምላክ ታማኝ ፍቅርና ምሕረት ትልቅ ትምህርት አግኝቷል። ተሞክሮው ልብ የሚነካ ነው።

የሚክያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ ትንቢት ይሖዋ ከእኛ የሚጠብቀው ነገር ምክንያታዊና እኛን የሚጠቅመን ነገር እንደሆነ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።

የናሆም መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ናሆም የተናገረው ትንቢት ይሖዋ ሁልጊዜ ቃሉን እንደሚጠብቅ እንዲሁም ሰላምና መዳን ለሚፈልጉ ሰዎች በመንግሥቱ አማካኝነት ማጽናኛ እንደሚሰጣቸው እርግጠኞች እንድንሆን ይረዳናል።

የዕንባቆም መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋ ሕዝቦቹን የሚያድንበትን ትክክለኛ ጊዜና መንገድ እንደሚያውቅ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

የሶፎንያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የይሖዋ ቀን እንደማይመጣ አድርገን ማሰብ የሌለብን ለምንድን ነው?

የሐጌ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የራስን ጥቅም ከማሳደድ ይልቅ የይሖዋን አምልኮ ማስቀደም ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልጽ ትንቢት

የዘካርያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በመንፈስ መሪነት የተነገሩ ትንቢቶች በጥንት ጊዜ የነበሩ የአምላክ አገልጋዮችን አበረታተዋቸዋል። እነዚህ ትንቢቶች አምላክ በዛሬው ጊዜም እንደሚደግፈን ያረጋግጣሉ።

የሚልክያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የሚልክያስ መጽሐፍ የአምላክን የማይለዋወጡ መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዲሁም የይሖዋን ምሕረትና ፍቅር ጎላ አድርጎ የሚገልጽ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ ነው። ትንቢቱ በዛሬ ጊዜም የሚሠሩ ጠቃሚ ትምህርቶችን ይዟል።

የማቴዎስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ከአራቱ ወንጌሎች መጀመሪያ ከተጻፈው ከዚህ መጽሐፍ ጋር የተያያዙ አንዳንድ መረጃዎችን ተመልከት።

የማርቆስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ከአራቱ ወንጌሎች ውስጥ አጭሩ የሆነው የማርቆስ ወንጌል፣ ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሲሆን ምን ነገሮችን እንደሚያከናውን የሚጠቁሙ ዘገባዎችን ይዟል።

የሉቃስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የሉቃስ ወንጌል ምን ለየት ያሉ መረጃዎችን ይዟል?

የዮሐንስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የዮሐንስ መጽሐፍ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር፣ ትሕትና በማሳየት ረገድ የተወውን ምሳሌ እንዲሁም የአምላክ መንግሥት ንጉሥ የሚሆነው መሲሕ መሆኑን ጎላ አድርጎ ይገልጻል።

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጥንት የነበሩት ክርስቲያኖች በሁሉም ብሔራት ውስጥ ያሉ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ በከፍተኛ ቅንዓት ሰብከዋል። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ለአገልግሎት ያለህ ቅንዓትና ጉጉት እንዲጨምር ይረዳሃል።

የሮም መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋ የማያዳላ መሆኑንና በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የሚያጎላ በመንፈስ መሪነት የተጻፈ መጽሐፍ።

የ1 ቆሮንቶስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት የጻፈው ደብዳቤ ስለ አንድነት፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕና እንዲሁም በትንሣኤ ስለ ማመን ይናገራል።

የ2 ቆሮንቶስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

“የመጽናናት ሁሉ አምላክ” የሆነው ይሖዋ አገልጋዮቹን ያበረታታቸዋል እንዲሁም ያጸናቸዋል።

የገላትያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ተመርቶ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩ ክርስቲያኖች የሰጠው ምክር ያን ጊዜ ጠቃሚ እንደነበረ ሁሉ በዛሬው ጊዜም ጠቃሚ ነው። ምክሩ ሁሉም ክርስቲያኖች ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ይረዳል።

የኤፌሶን መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ መጽሐፍ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ሰላምና አንድነት የማስፈን ዓላማ እንዳለው ይገልጻል።

የፊልጵስዩስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ፈተና ሲደርስብን መጽናታችን ሌሎችም ጸንተው እንዲቆሙ ያበረታታቸዋል።

የቆላስይስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የተማርነውን ነገር በሥራ ላይ በማዋል፣ እርስ በርሳችን በነፃ ይቅር በመባባል እንዲሁም የኢየሱስን ሥልጣን በመቀበል ይሖዋን ማስደሰት እንችላለን።

የ1 ተሰሎንቄ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በመንፈሳዊ ነቅተን መኖር፣ ‘ሁሉንም ነገር መመርመር፣’ ‘ዘወትር መጸለይና’ ‘እርስ በርስ መበረታታት’ ያስፈልገናል።

የ2 ተሰሎንቄ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጳውሎስ፣ ወንድሞች ከይሖዋ ቀን መምጣት ጋር በተያያዘ የነበራቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ አስተካክሏል፤ እንዲሁም ወንድሞች በእምነት ጸንተው እንዲቆሙ አበረታቷል።

የ1 ጢሞቴዎስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጳውሎስ 1 ጢሞቴዎስን የጻፈው የጉባኤ አሠራሮችን ግልጽ ለማድረግ እንዲሁም ከሐሰት ትምህርትና ከገንዘብ ፍቅር የመራቅን አስፈላጊነት ለማስገንዘብ ነው።

የ2 ጢሞቴዎስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጳውሎስ አገልግሎቱን በተሟላ ሁኔታ እንዲፈጽም ጢሞቴዎስን አበረታቶታል።

የቲቶ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጳውሎስ ለቲቶ የጻፈው ደብዳቤ በቀርጤስ ጉባኤ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ለማስተካከል የሚረዳና ሽማግሌዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መንፈሳዊ ብቃቶችን ግልጽ የሚያደርግ ነው።

የፊልሞና መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይህ አጭር ሆኖም ትልቅ ቁም ነገር የያዘ ደብዳቤ ስለ ትሕትና፣ ደግነትና ይቅር ባይነት ጠቃሚ ምክር ይዟል።

የዕብራውያን መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የክርስቲያኖች አምልኮ ከቤተ መቅደሶችና ከእንስሳት መሥዋዕት እጅግ በላቁ ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነው።

የያዕቆብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ያዕቆብ ክርስቲያኖች ሊከተሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ለማስረዳት ዘይቤያዊ አነጋገሮችን ተጠቅሟል።

የ1 ጴጥሮስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጴጥሮስ የጻፈው የመጀመሪያ ደብዳቤ ንቁ እንድንሆንና የሚያስጨንቁንን ነገሮች በሙሉ በይሖዋ ላይ እንድንጥል የሚያበረታታ ነው።

የ2 ጴጥሮስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ጴጥሮስ የጻፈው ሁለተኛ ደብዳቤ በቅርቡ የሚመጡትን አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር ስንጠባበቅ ታማኞች መሆን እንዳለብን የሚያበረታታ ነው።

የ1 ዮሐንስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የዮሐንስ ደብዳቤ ከፀረ ክርስቶሶች መራቅ እንዳለብን የሚያስጠነቅቅ ሲሆን ፍቅር የሚያደርጋቸውንና የማያደርጋቸውን ነገሮች ማስተዋል እንድንችልም ይረዳናል።

የ2 ዮሐንስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ዮሐንስ የጻፈው ሁለተኛው ደብዳቤ በእውነት ውስጥ መመላለስ እንዳለብንና ከአሳቾች መጠንቀቅ እንዳለብን የሚያሳስብ ነው።

የ3 ዮሐንስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ዮሐንስ የጻፈው ሦስተኛው ደብዳቤ ክርስቲያኖች የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ማሳየት እንዳለባቸው ያበረታታል።

የይሁዳ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሁዳ የክርስቲያን ጉባኤን አባላትን ለማታለልና ለመበከል የሚጥሩ ሰዎች የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ምን እንደሆኑ በዝርዝር ገልጻል።

የራእይ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት አስደናቂ ራእዮች አምላክ ለሰው ልጆችና ለምድር ያለውን ዓላማ በመንግሥቱ አማካኝነት የሚፈጽመው እንዴት እንደሆነ ይገልጻሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ማስተዋወቂያ

እያንዳንዱ መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ ጭብጥ ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በሚተዳደረው የአምላክ መንግሥት አማካኝነት ከሚረጋገጠው የይሖዋ ስም ቅድስና ጋር የሚያያዘው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

እነዚህንስ አይተሃቸዋል?

መጻሕፍትና ብሮሹሮች

መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?