በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 76

ምን ይሰማሃል?

ምን ይሰማሃል?

(ዕብራውያን 13:15)

  1. 1. ስትሰብክ ምን ተሰማህ?

    ሰዎችን ስታስተምር፣

    ልባቸውን ለመንካት

    ያቅምህን ስትጥር?

    ምርጥህን ስትሰጠው

    አምላክ ያሳካልሃል።

    ልበ ቅን የሆኑትን

    እሱ ያውቃቸዋል።

    (አዝማች)

    ደስ ይለናል መስጠታችን

    ላምላክ ሁለንተናችንን።

    ኑ! እናቅርብ የውዳሴ

    መሥዋዕት ሁልጊዜ።

  2. 2. ያኔ ምን ተሰማህ?

    ቃሉን የነገርካቸው

    እውነትን ሲቀበሉ

    ተነክቶ ልባቸው?

    አንዳንዶች ቢርቁም፣

    ሌሎች ከ’ውነት ቢወጡም

    በስብከቱ ሥራችን

    መጽናት ነው ምርጫችን።

    (አዝማች)

    ደስ ይለናል መስጠታችን

    ላምላክ ሁለንተናችንን።

    ኑ! እናቅርብ የውዳሴ

    መሥዋዕት ሁልጊዜ።

  3. 3. ስታውቅ ምን ተሰማህ?

    አምላክ እንደሚረዳህ፤

    እንደሰጠህ ባደራ

    የምትሠራው ሥራ?

    ለዛ ባለው መንገድ

    ግን በድፍረት እንስበክ፤

    ሥራው በቅርብ ያበቃል፤

    ቅኖችን እንፈልግ።

    (አዝማች)

    ደስ ይለናል መስጠታችን

    ላምላክ ሁለንተናችንን።

    ኑ! እናቅርብ የውዳሴ

    መሥዋዕት ሁልጊዜ።

(በተጨማሪም ሥራ 13:48⁠ን፣ 1 ተሰ. 2:4⁠ን እና 1 ጢሞ. 1:11⁠ን ተመልከት።)