በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 75

“እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

“እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

(ኢሳይያስ 6:8)

  1. 1. አምላክ ዛሬ ስሙ ጠፍቷል፤

    ጨካኝ ተደርጎ ተቆጥሯል።

    ‘ደካማ ነው’ ብለውታል፤

    ሞኝም “አምላክ የለም” ይላል።

    ማን ነው ጥብቅና ’ሚቆመው?

    አምላክን የሚያወድሰው?

    (አዝማች 1)

    ‘ጌታ ’ነሆኝ! እኔን ላከኝ፤

    ላወድስህ ዝግጁ ነኝ።

    ከዚህ በላይ ምን ክብር ሊገኝ፤

    እነሆኝ! እኔን ላከኝ!’

  2. 2. አይፈሩም ሲገዳደሩት፣

    ‘እርምጃ አይወስድም’ ሲሉት።

    ጣዖት ሠርተው አመለኩ፤

    ቦታውን በቄሳር ተኩ።

    ማን ሄዶ ያስጠንቅቃቸው?

    “ጥፋት መጣ” ይበላቸው?

    (አዝማች 2)

    ‘ጌታ ’ነሆኝ! እኔን ላከኝ፤

    ለመናገር ድፍረት አለኝ።

    ከዚህ በላይ ምን ክብር ሊገኝ፤

    እነሆኝ! እኔን ላከኝ!’

  3. 3. ዓለም በክፋት ተሞልቷል፤

    ገሮች አዝነው አልቅሰዋል።

    ሰላም ’ሚሰጠውን እውነት፣

    ያስፈልጋቸዋል ማግኘት።

    ማን ነው ሄዶ ’ሚያጽናናቸው?

    መንገዱን የሚያሳያቸው?

    (አዝማች 3)

    ‘ጌታ ’ነሆኝ! እኔን ላከኝ፤

    ለማስተማር ት’ግሥት አለኝ።

    ከዚህ በላይ ምን ክብር ሊገኝ፤

    እነሆኝ! እኔን ላከኝ!’

(በተጨማሪም መዝ. 10:4⁠ን እና ሕዝ. 9:4⁠ን ተመልከት።)