መዝሙር 45
በልቤ የማሰላስለው ነገር
-
1. በልቤ ’ማሰላስለው፣
ቀኑን ሙሉ የማስበው፣
አንተን ከልብ ያስደስትህ፤
ሁሌም ያጽናኝ በመንገድህ።
ችግር፣ ሐሳብ ሲያስጨንቀኝ፣
ሌሊት እንቅልፌን ሲነሳኝ፣
ያኔ ስላንተ ላውጠንጥን፤
ቀና ሐሳብ እንዲኖረኝ።
-
2. ንጹሕ፣ እውነት የሆነውን፣
በጎ ነገር ያለበትን፣
ስለ ’ነዚህ ማሰብ ሁሌ፣
ሰላም ’ሚሰጥ ይሁን ለኔ።
አንተ ሐሳብህ ድንቅ ነው፤
ቁጥሩስ ምንኛ ብዙ ነው!
ይህን አሰላስላለሁ፤
ትኩረቴም በ’ነዚህ ላይ ነው።
(በተጨማሪም መዝ. 49:3፤ 63:6፤ 139:17, 23ን፣ ፊልጵ. 4:7, 8ን እና 1 ጢሞ. 4:15ን ተመልከት።)