በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 44

የተቸገረ ሰው ጸሎት

የተቸገረ ሰው ጸሎት

(መዝሙር 4:1)

  1. 1. አምላክ ሆይ፣ ‘ጸሎቴን ስማ’

    ብዬ እጮኻለሁ።

    ቆስያለሁ፤ ሸክሜ ከብዷል፤

    በጣም ደክሜያለሁ።

    ይሰማኛል ዋጋ ’ንዳጣሁ፤

    ተስፋም ቆርጫለሁ።

    አጽናኙ አምላክ ይሖዋ፣

    አስብልኝ ምነው?

    (አዝማች)

    ቀና አ’ርገኝ፤ ልጽና እርዳኝ።

    ተስፋው እውን ይሁንልኝ።

    ሳዝን ቶሎ ድረስልኝ።

    አንተ ኃይሌን አድስልኝ።

  2. 2. ቃልህ ያጽናናኛል፤

    ስደክም ያበረታኛል።

    ውስጤን መግለጽ ሳልችል ስቀር

    ስሜቴን ይጋራል።

    ቃልህ ውስጥ ያለው እውነት

    እምነቴን ይገንባልኝ።

    ፍቅርህ ከልቤ ይበልጥ

    ታላቅ መሆኑም ይግባኝ።

    (አዝማች)

    ቀና አ’ርገኝ፤ ልጽና እርዳኝ።

    ተስፋው እውን ይሁንልኝ።

    ሳዝን ቶሎ ድረስልኝ።

    አንተ ኃይሌን አድስልኝ።

(በተጨማሪም መዝ. 42:6⁠፤ 119:28⁠ን፣ ሮም 8:26⁠ን፣ 2 ቆሮ. 4:16⁠ን እና 1 ዮሐ. 3:20⁠ን ተመልከት።)