በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 4

“ይሖዋ እረኛዬ ነው”

“ይሖዋ እረኛዬ ነው”

(መዝሙር 23)

  1. 1. ይሖዋ እረኛዬ ነው፤

    እሱን ነው ’ምከተለው።

    የልቤን መሻት በደንብ ያውቃል፤

    ፍላጎቴን ያሟላል።

    ወደ ’ረፍት ወንዝ ይወስደኛል፤

    ነፍሴንም ያድሳታል።

    እሱ ነው በፍቅሩ የሚመራኝ፣

    ሰላም፣ ’ረፍት የሚሰጠኝ።

    እሱ ነው በፍቅሩ ’ሚመራኝ፣

    ሰላም፣ ’ረፍት የሚሰጠኝ።

  2. 2. መንፈስ ያድሳል ት’ዛዝህ፤

    ሰላም ይሰጣል ሕግህ፤

    ለስምህ ስትል አ’ተወኝም፤

    እንድባዝን አትፈቅድም።

    በጨለማ ውስጥ ብጓዝም

    ይመራኛል በትርህ።

    አልፈራም አንተ ’ስካለህ ከጎኔ፤

    አምላኬ ነህ ወዳጄ።

    አልፈራም እስካለህ ከጎኔ፤

    አምላኬ ነህ ወዳጄ።

  3. 3. እረኛዬ ይሖዋ ሆይ፣

    ምራኝ ልከተል አንተን።

    እረፍት፣ ብርታት የምትሰጠኝ

    አንተ ነህ የምትመራኝ።

    ዘላለማዊ አምላክ ነህ

    የምተማመንብህ።

    በፍቅርህ እንድኖር ነው ጸሎቴ፤

    እስካለሁ በሕይወቴ።

    በፍቅርህ ’ንድኖር ነው ጸሎቴ፤

    እስካለሁ በሕይወቴ።

(በተጨማሪም መዝ. 28:9⁠ን እና 80:1⁠ን ተመልከት።)