በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 3

ኃይላችን፣ ተስፋችን፣ ትምክህታችን

ኃይላችን፣ ተስፋችን፣ ትምክህታችን

(ምሳሌ 14:26)

  1. 1. ይሖዋ ሆይ፣ ተስፋ ሰጠኸን፤

    ከፍ አ’ርገን ’ምናየው።

    ወደር የሌለው ተስፋ ነው፤

    ዓለም ሁሉ ይስማው።

    ሆኖም የሕይወት ውጣ ውረድ

    አንዳንዴ ይከብደናል፤

    የሰጠኸን ብሩህ ተስፋም

    ይጨልምብናል።

    (አዝማች)

    ኃይላችን፣ ተስፋችን፣

    ትምክ’ታችን ነህ።

    ሁሌም ትደግፈናለህ።

    ቃልህን ስንሰብክ

    ልበ ሙሉ ነን፤

    መታመኛችን አንተ ነህ።

  2. 2. አምላክ ሆይ፣ ችግር ሲያጋጥመን

    እንዳንረሳ እርዳን፤

    ከጎናችን እንደምትሆን፣

    እንደምታጽናናን።

    ይህን ስናስብ ደስ ይለናል፤

    ኃይላችን ይታደሳል።

    ስለ ስምህ ለመናገር

    ድፍረት ይኖረናል።

    (አዝማች)

    ኃይላችን፣ ተስፋችን፣

    ትምክ’ታችን ነህ።

    ሁሌም ትደግፈናለህ።

    ቃልህን ስንሰብክ

    ልበ ሙሉ ነን፤

    መታመኛችን አንተ ነህ።

(በተጨማሪም መዝ. 72:13, 14⁠ን፣ ምሳሌ 3:5, 6, 26⁠ን እና ኤር. 17:7⁠ን ተመልከት።)