በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 151

አምላክ ይጣራል

አምላክ ይጣራል

(ኢዮብ 14:13-15)

  1. 1. የሰው ሕይወት ጠፊ ነው እንፋሎት፤

    ዛሬ ታይቶ ለቅጽበት።

    ስንሞት ሁሉም ነገር ያከትማል፤

    እንባ፣ ሐዘን ይነግሣል።

    ሰው ይነሳል ወይ አንዴ ከሞተ?

    አምላክ ቃል ገብቶልናል፦

    (አዝማች)

    ይጣራል፤ ይመልሳሉ፤

    በሕይወት ይኖራሉ።

    የ’ጁ ሥራዎች ናቸው፤

    ይጓጓል ሊያስነሳቸው።

    እንግዲያው እምነት ይኑርህ፤

    ይሖዋ ’ንደሚያስነሳህ።

    የ’ጁ ሥራ ስለሆ’ን

    ዘላለም እ’ኖራለን።

  2. 2. ያምላካችን ወዳጆች ቢሞቱም

    በፍጹም አይረሱም።

    ያንቀላፉ፣ ባምላክ መዝገብ ያሉ፣

    ቃል ገብቷል ይነቃሉ።

    ከዚያም አንድ ላይ እንኖራለን

    በገነት ለዘላለም።

    (አዝማች)

    ይጣራል፤ ይመልሳሉ፤

    በሕይወት ይኖራሉ።

    የ’ጁ ሥራዎች ናቸው፤

    ይጓጓል ሊያስነሳቸው።

    እንግዲያው እምነት ይኑርህ፤

    ይሖዋ ’ንደሚያስነሳህ።

    የ’ጁ ሥራ ስለሆ’ን

    ዘላለም እ’ኖራለን።

(በተጨማሪም ዮሐ. 6:40⁠፤ 11:11, 43⁠ን እና ያዕ. 4:14⁠ን ተመልከት።)