በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 150

ትድኑ ዘንድ አምላክን ፈልጉ

ትድኑ ዘንድ አምላክን ፈልጉ

(ሶፎንያስ 2:3)

  1. 1. ብሔራት ዓመፁ፤

    ባምላክ ልጅ ላይ ተነሱ።

    የሰው አገዛዝ ያከትማል፤

    ይሖዋ ፍርዱን ሰጥቷል።

    ገዢዎች በቃቸው፤

    ያምላክ መንግሥት ተራ ነው።

    ’የሱስ ጠላቶቹን ያደቃል፤

    ጊዜውም በጣም ቀርቧል።

    (አዝማች)

    እንድታገኙ መዳንን

    በ’ምነት ፈልጉት አምላክን።

    ጽድቁን ፈልጉ፤

    ታማኞች ሁኑ፤

    ልዕልናውን ደግፉ።

    ያኔ ክንዱን ታያላችሁ፤

    ሲታደጋችሁ።

  2. 2. ምሥራቹ ላለም

    እየተሰበከ ነው፤

    እኛ ግብዣ ’ናቀርባለን፤

    ምርጫው ግን የነሱ ነው።

    ፈተናው ቢከብድም

    በፍርሃት አንዋጥም።

    ይሖዋ ሕዝቡን ይጠብቃል፤

    ስንጮኽ ይሰማናል።

    (አዝማች)

    እንድታገኙ መዳንን

    በ’ምነት ፈልጉት አምላክን።

    ጽድቁን ፈልጉ፤

    ታማኞች ሁኑ፤

    ልዕልናውን ደግፉ።

    ያኔ ክንዱን ታያላችሁ፤

    ሲታደጋችሁ።

(በተጨማሪም 1 ሳሙ. 2:9⁠ን፣ መዝ. 2:2, 3, 9⁠ን፣ ምሳሌ 2:8⁠ን እና ማቴ. 6:33⁠ን ተመልከት።)