በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 104

የአምላክ ስጦታ የሆነው መንፈስ ቅዱስ

የአምላክ ስጦታ የሆነው መንፈስ ቅዱስ

(ሉቃስ 11:13)

  1. 1. ልዑሉ አምላክ፣ መሐሪው አባት፣

    ከልባችን ይበልጥ ታላቅ ነህ።

    ሸክማችንን ቀላል አ’ርግልን፤

    ’ባክህ ስጠን አጽናኝ መንፈስህን።

  2. 2. ልናንጸባርቅ አንችል ክብርህን፤

    ብዙ ጊዜ እንስታለን።

    አምላክ ሆይ፣ እንማጸንሃለን፣

    መንፈስህ በየቀኑ ’ንዲመራን።

  3. 3. ስንዝል፣ ስንደክም፣ ተስፋ ስንቆርጥ፣

    መንፈስህ ነው እኛን ’ሚያድሰን።

    እንደ ንስር መብረር እንድንችል፣

    ኃያል ቅዱስ መንፈስህን ስጠን።

(በተጨማሪም መዝ. 51:11⁠ን፣ ዮሐ. 14:26⁠ን እና ሥራ 9:31⁠ን ተመልከት።)