በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 103

እረኞች—ስጦታ የሆኑ ወንዶች

እረኞች—ስጦታ የሆኑ ወንዶች

(ኤፌሶን 4:8)

  1. 1. አምላካችን በደግነቱ

    እረኞች ሰጥቶናል፤

    ምሳሌ ሆነው በማገልገል

    መንገድ ይመሩናል።

    (አዝማች)

    አምላክ ሰጥቶናል ታማኝ ወንዶች፣

    እውነተኛ እረኞች።

    ለመንጋው ’ሚጨነቁ ናቸው፤

    ምንጊዜም አድንቋቸው።

  2. 2. በርኅራኄ ይይዙናል፣

    በፍቅር በመምራት።

    ስንጎዳ ይጠግኑናል፣

    በቃል በማጽናናት።

    (አዝማች)

    አምላክ ሰጥቶናል ታማኝ ወንዶች፣

    እውነተኛ እረኞች።

    ለመንጋው ’ሚጨነቁ ናቸው፤

    ምንጊዜም አድንቋቸው።

  3. 3. ከአምላክ መንገድ እንዳንወጣ፣

    ምክር ይሰጡናል።

    ሁሌ እንድናገለግለው፣

    ያበረታቱናል።

    (አዝማች)

    አምላክ ሰጥቶናል ታማኝ ወንዶች፣

    እውነተኛ እረኞች።

    ለመንጋው ’ሚጨነቁ ናቸው፤

    ምንጊዜም አድንቋቸው።

(በተጨማሪም ኢሳ. 32:1, 2⁠ን፣ ኤር. 3:15⁠ን፣ ዮሐ. 21:15-17⁠ን እና ሥራ 20:28⁠ን ተመልከት።)