በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የባሕር ኧርቺን ራሱን የሚሞርድ ጥርስ

የባሕር ኧርቺን ራሱን የሚሞርድ ጥርስ

ንድፍ አውጪ አለው?

የባሕር ኧርቺን ራሱን የሚሞርድ ጥርስ

● የባሕር ኧርቺን በአምስት ጥርሶቹ በመጠቀም አለቶችን ቦርቡሮ የሚደበቅበትን ጎሬ ይሠራል። ኧርቺኑ በጥርሱ ድንጋዩን የሚሰረስርና የሚፍቅ ቢሆንም ጥርሱ አይዶለዱምም። በዩናይትድ ስቴትስ የዊስኮንሰን ማዲሰን ዩኒቨርስቲ የፊዚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፑፓ ጊልበርት “ከምናውቃቸውና ለመቁረጥ ወይም ለመሰርሰር ከምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች መካከል ስለ የትኛውም ቢሆን እንዲህ ማለት አንችልም” ብለዋል። የባሕር ኧርቺን ጥርስ የማይዶለዱም የሆነበት ሚስጥር ምንድን ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የባሕር ኧርቺን ጥርሶች የተሠሩት አንዳቸው በሌላው ላይ ከተነባበሩ ክሪስታሎች ነው። ይሁን እንጂ “ጥርሶቹ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ሽርፍ እንዲሉ ሆነው” እንደተሠሩ ጊልበርት ገልጸዋል። በእነዚህ ቦታዎች ላይ ያለው የጥርሱ ክፍል ጠንካራ አይደለም፤ ቴምብርን በቀላሉ ለመቁረጥ ከሚያስችለው በዙሪያው ካለው የተበሳሳ ወረቀት ጋር ይመሳሰላል። በመሆኑም የዶለዶመው የጥርሱ ክፍል ጠንካራ ባልሆኑት ቦታዎች ላይ በቀላሉ ሲሸረፍ በምትኩ አዲስና ስል የሆነ ጥርስ ብቅ ይላል። ጥርሱ ከውስጥ በኩል እያደገ ሲሄድ ጫፉ ላይ ደግሞ ራሱን ስለሚሞርድ ፈጽሞ አይዶለዱምም። ጊልበርት፣ የኧርቺን ጥርስ “በተፈጥሮ ውስጥ ካሉ ራሳቸውን የሚሞርዱ ጥቂት ነገሮች አንዱ” እንደሆነ ገልጸዋል።

ራሱን የሚሞርደው የኧርቺን ጥርስ ይህን የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ማወቅ የመገልገያ መሣሪያዎችን ለሚሠሩ ሰዎች ትልቅ ትርጉም አለው። ይህን ማወቃቸው ራሳቸውን የሚሞርዱ የመገልገያ መሣሪያዎችን ለመፈልሰፍ እንደሚያስችላቸው ይታመናል። ጊልበርት “ቁልፉ የባሕር ኧርቺን የሚጠቀምበትን ዘዴ ማወቁ ላይ ነው” ይላሉ።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ራሱን የሚሞርደው የባሕር ኧርቺን ጥርስ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሰንጠረዥ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

የሚያድግ ጥርስ

የካልሽየም ካርቦኔት ሽፋን

የተሞረደ ጥርስ

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የባሕር ኧርቺን

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

አምስት ጥርሶች

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Both photos: Courtesy of Pupa Gilbert/University of Wisconsin-Madison