በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ጸሎት ሰሚ” የሆነው አምላክ የእኛን ጸሎት መስማት ያስደስተዋል።—መዝሙር 65:2

የፈጣሪን በረከት ለማግኘት አዘውትረህ ጸልይ

የፈጣሪን በረከት ለማግኘት አዘውትረህ ጸልይ

አምላክ ለሰው ልጆች ልዩ ስጦታ ሰጥቷቸዋል፤ ይህም ሐሳባቸውንና ስሜታቸውን በጸሎት ለእሱ የመግለጽ መብት ነው። ነቢዩ ዳዊት “ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው ወደ አንተ ይመጣል” በማለት ጸልዮአል። (መዝሙር 65:2) ይሁንና አምላክ ጸሎታችንን እንዲሰማንና እንዲባርከን ምን ዓይነት ጸሎት ማቅረብ ይኖርብናል?

በትሕትና እና ከልብህ ጸልይ

በግልህ ወደ አምላክ ስትጸልይ ልብህን በፊቱ ማፍሰስ ወይም የውስጥ ስሜትህን ለእሱ መንገር ትችላለህ። (መዝሙር 62:8) ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ከልብህ የምታቀርበውን ጸሎት ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል።

ወደ አምላክ ስትጸልይ በስሙ ተጠቀም

አምላክ ብዙ የማዕረግ ስሞች ቢኖሩትም የግል ስሙ አንድ ብቻ ነው። ፈጣሪያችን “እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው” ብሏል። (ኢሳይያስ 42:8) ይሖዋ የሚለው ስም በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ወደ 7,000 ጊዜ ገደማ ይገኛል። በርካታ ነቢያት አምላክን የጠሩት በግል ስሙ ነው። አብርሃም “ይሖዋ እባክህ . . . አሁንም ልናገር” የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። (ዘፍጥረት 18:30) እኛም ስንጸልይ፣ ይሖዋ የተባለውን የአምላክ ስም መጠቀም ይኖርብናል።

በቋንቋህ ጸልይ

የምንጠቀምበት ቋንቋ ምንም ይሁን ምን፣ አምላክ ሐሳባችንን እና ስሜታችንን ይረዳል። ቃሉ የሚከተለውን ማረጋገጫ ይሰጠናል፦ “አምላክ [አያዳላም]፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

ይሁን እንጂ የአምላክን በረከት ለማግኘት ከጸሎት በተጨማሪ ማድረግ የሚጠበቅብን ነገር አለ። ይህ ምን እንደሆነ በቀጣዮቹ ርዕሶች ላይ እንመለከታለን።