‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’

ይህ መጽሐፍ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ስለነበረው የክርስቲያን ጉባኤ አመሠራረት እንዲሁም ይህ ዘገባ ለእኛ ምን ትርጉም እንዳለው ያወሳል።

ካርታዎች

በዛሬው ጊዜ በተለምዶ ቅድስቲቱ ምድር ተብሎ የሚጠራውን ቦታ እና ሐዋርያው ጳውሎስ ሚስዮናዊ ጉዞ ያደረገባቸውን ቦታዎች የሚያሳይ ካርታ።

ከበላይ አካሉ የተላከ ደብዳቤ

ስለ አምላክ መንግሥት ‘በሚገባ መመሥከራችንን’ ስንቀጥል አምላክ እንደሚደግፈን እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 1

“ሂዱና . . . ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ”

ኢየሱስ የመንግሥቱ መልእክት ለሁሉም ብሔራት እንደሚሰበክ ተናግሯል። ይህ ትንቢት እየተፈጸመ ያለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 2

“ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ”

ኢየሱስ የስብከቱን ሥራ በግንባር ቀደምትነት እንዲያከናውኑ ሐዋርያቱን ያዘጋጃቸው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 3

“በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”

የአምላክ ቅዱስ መንፈስ በክርስቲያን ጉባኤ አመሠራረት ላይ ምን ሚና ተጫውቷል?

ምዕራፍ 4

“ያልተማሩና ተራ ሰዎች”

ሐዋርያት ድፍረት የሚጠይቅ ነገር አድርገዋል፤ ይሖዋም ባርኳቸዋል።

ምዕራፍ 5

“አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል”

ሐዋርያት የወሰዱት አቋም ለሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች አርዓያ የሚሆን ነው።

ምዕራፍ 6

‘ጸጋና ኃይል የተሞላው እስጢፋኖስ’

እስጢፋኖስ በአይሁዳውያን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ በድፍረት ከሰጠው ምሥክርነት ምን እንማራለን?

ምዕራፍ 7

“ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች” ማወጅ

ፊልጶስ ወንጌላዊ በመሆን ረገድ ግሩም ምሳሌ ትቶልናል።

ምዕራፍ 8

ጉባኤው “ሰላም አገኘ”

ሳኦል ርኅራኄ የሌለው አሳዳጅ ነበር፤ አሁን ቀናተኛ የክርስቶስ አገልጋይ ሆነ።

ምዕራፍ 9

‘አምላክ አያዳላም’

ክርስቲያኖች ላልተገረዙ አሕዛብም መስበክ ጀመሩ።

ምዕራፍ 10

“የይሖዋ ቃል . . . እየተስፋፋ ሄደ”

ጴጥሮስ ከእስር ነፃ ወጣ፤ ስደት ምሥራቹ እንዳይስፋፋ ማገድ አልቻለም።

ምዕራፍ 11

“በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”

ጳውሎስ ተቃዋሚዎችንና መልእክቱን የማይቀበሉ ሰዎችን የያዘበት መንገድ ግሩም ምሳሌ ይሆነናል።

ምዕራፍ 12

“ከይሖዋ ባገኙት ሥልጣን በድፍረት” ተናገሩ

ጳውሎስና በርናባስ ትሕትና፣ ጽናትና ሁኔታዎችን እንደ አመጣጣቸው የማስተናገድ ችሎታ አሳይተዋል።

ምዕራፍ 13

“የጦፈ ክርክር” ተነሳ

አወዛጋቢው የግርዘት ጉዳይ የበላይ አካሉ ውሳኔ እንዲያደርግበት ቀረበ።

ምዕራፍ 14

“በአንድ ልብ ወሰንን”

የበላይ አካሉ ከግርዘት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውሳኔ ላይ የደረሰው እንዴት ነው? ውሳኔው፣ ጉባኤውን አንድ ያደረገውስ እንዴት ነው? ይህ ምዕራፍ ስለ እነዚህ ጉዳዮች ያብራራል።

ምዕራፍ 15

‘ጉባኤዎችን ማበረታታት’

ተጓዥ አገልጋዮች፣ ጉባኤዎች በእምነት ጸንተው እንዲቆሙ ይረዳሉ።

ምዕራፍ 16

“ወደ መቄዶንያ ተሻገር”

የአገልግሎት ምድብ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆንና ስደትን በደስታ መቋቋም በረከት ያስገኛል።

ምዕራፍ 17

“ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነሱ ጋር ተወያየ”

ጳውሎስ በተሰሎንቄና በቤርያ ለሚኖሩ አይሁዳውያን በሚገባ መሠከረ።

ምዕራፍ 18

“አምላክን እንዲፈልጉትና . . . እንዲያገኙት”

ጳውሎስ ከአድማጮቹ ጋር የሚያስማማውን ነጥብ ማግኘቱ የትኞቹን የስብከት አጋጣሚዎች ከፍቶለታል?

ምዕራፍ 19

“መናገርህን ቀጥል እንጂ ዝም አትበል”

ጳውሎስ በቆሮንቶስ ያከናወነው ነገር ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ ስለ መመሥከር ምን ያስተምረናል?

ምዕራፍ 20

ተቃውሞ ቢኖርም “የይሖዋ ቃል . . . እየተስፋፋና እያሸነፈ ሄደ”

አጵሎስና ጳውሎስ ምሥራቹ እየተስፋፋ እንዲሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ እንመልከት።

ምዕራፍ 21

‘ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ ነኝ’

ጳውሎስ አገልግሎቱን ሲያከናውን ያሳየው ቅንዓትና ለሽማግሌዎች የሰጠው ምክር።

ምዕራፍ 22

“የይሖዋ ፈቃድ ይሁን”

ጳውሎስ የአምላክን ፈቃድ ለመፈጸም ቆርጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ።

ምዕራፍ 23

“የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”

ጳውሎስ ለረብሻ በተሰበሰበው ሕዝብና በሳንሄድሪን ፊት ለእውነት ተሟገተ።

ምዕራፍ 24

“አይዞህ፣ አትፍራ!”

ጳውሎስ እሱን ለመግደል ከተጠነሰሰው ሴራ አምልጦ በፊሊክስ ፊት የመከላከያ መልስ አቀረበ።

ምዕራፍ 25

“ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!”

ጳውሎስ ለምሥራቹ ጥብቅና በመቆም ረገድ ምሳሌ ትቷል።

ምዕራፍ 26

“ከእናንተ አንድም ሰው አይጠፋም”

ጳውሎስ፣ የሚጓዝበት መርከብ አደጋ ሲያጋጥመው ጠንካራ እምነትና ለሰዎች ፍቅር እንዳለው አሳይቷል።

ምዕራፍ 27

“በሚገባ . . . መመሥከር”

ጳውሎስ በሮም ታስሮ እያለም መስበኩን አላቆመም።

ምዕራፍ 28

“እስከ ምድር ዳር ድረስ”

የይሖዋ ምሥክሮች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. የጀመሩትን ሥራ እያከናወኑ ነው።

የሥዕል ማውጫ

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ሥዕሎች ዝርዝር።