በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ቃል በቃል በስድስት ቀናት ውስጥ ነው ብለው ያምናሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ቃል በቃል በስድስት ቀናት ውስጥ ነው ብለው ያምናሉ?

 በፍጹም! የይሖዋ ምሥክሮች አምላክ ሁሉን ነገር እንደፈጠረ ያምናሉ። ያም ቢሆን በክሪኤሽኒዝም የሚያምኑ ሰዎች እንደሚሉት አምላክ እነዚህ ነገሮች የፈጠረው በስድስት ቀናት ውስጥ እንደሆነ አናምንም። ለምን? ምክንያቱም አብዛኞቹ የክሪኤሽኒዝም ንድፈ ሐሳቦች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫሉ። እስቲ ሁለት ምሳሌዎችን እንመልከት፦

  1.   የስድስቱ የፍጥረት ቀናት ርዝማኔ። አንዳንድ በክሪኤሽኒዝም የሚያምኑ ሰዎች ስድስቱ የፍጥረት ቀናት የ24 ሰዓት ርዝመት እንዳላቸው ያምናሉ። ይሁንና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቀን” የሚለው ቃል ረዘም ያለ ጊዜን ሊያመለክት ይችላል።​—ዘፍጥረት 2:4፤ መዝሙር 90:4

  2.   የምድር ዕድሜ። አንዳንድ በክሪኤሽኒዝም የሚያምኑ ሰዎች ምድር የተፈጠረችው ከጥቂት ሺህ ዓመታት በፊት እንደሆነ ያስተምራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ምድራችንን ጨምሮ መላው አጽናፈ ዓለም የተፈጠረው ከስድስቱ የፍጥረት ቀናት በፊት እንደሆነ ይናገራል። (ዘፍጥረት 1:1) በመሆኑም የይሖዋ ምሥክሮች ምድር የቢሊዮን ዓመታት ዕድሜ ባለቤት ልትሆን ትችላለች የሚለውን በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ ሐቅ አይቃወሙም።

 የይሖዋ ምሥክሮች በፍጥረት የሚያምኑ ቢሆንም ሳይንስን አይቃወሙም። ትክክለኛ ሳይንስና መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርስ እንደሚደጋገፉ ያምናሉ።