በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል?

የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 የአምላክ መንግሥት፣ ሁሉንም ሰብዓዊ መንግሥታት አጥፍቶ መላውን ምድር ይገዛል። (ዳንኤል 2:44፤ ራእይ 16:14) በዚህ ጊዜ የአምላክ መንግሥት . . .

  •   በራስ ወዳድነት በሌሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ክፉ ሰዎችን ያጠፋል። “ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይወገዳሉ።”—ምሳሌ 2:22

  •   ጦርነትን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። “[አምላክ] ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል።”—መዝሙር 46:9

  •   በምድር ላይ ብልጽግናን እና ሰላምን ያሰፍናል። “እያንዳንዱ ሰው በተከለው ወይንና በለስ ጥላ ሥር በሰላም ይኖራል፤ የሚያስፈራውም ነገር አይኖርም።”—ሚክያስ 4:4 የ1980 ትርጉም

  •   ምድርን ወደ ገነትነት ይለውጣል። “ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤ በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤ እንደ አደይም ያብባል።”—ኢሳይያስ 35:1

  •   እያንዳንዱ ሰው ትርጉም ያለውና አስደሳች ሥራ እንዲኖረው ያደርጋል። “[አምላክ የመረጣቸው ሰዎች] በእጃቸው ሥራ ለረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል። ድካማቸው በከንቱ አይቀርም።”—ኢሳይያስ 65:21-23

  •   በሽታን ያጠፋል። “‘ታምሜአለሁ’ የሚል አይኖርም።”—ኢሳይያስ 33:24

  •   እርጅናን ያስወግዳል። “ሥጋው እንደ ሕፃን ልጅ ገላ ይታደሳል፤ ወደ ወጣትነቱም ዘመን ይመለሳል።”—ኢዮብ 33:25

  •   የሞቱ ሰዎችን ያስነሳል። ‘በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ የኢየሱስን ድምፅ ሰምተው ይወጣሉ።’—ዮሐንስ 5:28, 29