በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 16, 2021
ዓለም አቀፋዊ ዜና

በJW.ORG መነሻ ገጽ ላይ የሚወጡ ወቅታዊ ርዕሶች ያስገኙት ግሩም ውጤት

በJW.ORG መነሻ ገጽ ላይ የሚወጡ ወቅታዊ ርዕሶች ያስገኙት ግሩም ውጤት

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በ​jw.org ላይ የምናስተዋውቃቸውን ርዕሶች በአገልግሎትና በግል ጥናታቸው ላይ እየተጠቀሙባቸው ነው። ይህም በርካታ ግሩም ውጤቶችን አስገኝቷል። አንዳንድ ተሞክሮዎችን እስቲ እንመልከት።

በካናዳ የሚያገለግል አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች ሪፖርት እንዳደረገው ወረርሽኙ ከጀመረ በኋላ በነበሩት ጥቂት ወራት በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ አስፋፊዎች ውስጥ ሦስት አራተኛ የሚሆኑት “ብቸኝነትን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ” የሚለውን ርዕስ በአገልግሎት ላይ ተጠቅመውበታል። ለምሳሌ ያህል፣ አንዲት እህት የዚህን ርዕስ ሊንክ ለስድስት የሥራ ባልደረቦቿ ልካላቸው ነበር። አንዳንዶቹ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

ከባለቤቷ ጋር በወረዳ ሥራ የምትካፈል በቶጎ የምትኖር አንዲት እህት ደግሞ “በራእይ መጽሐፍ ላይ የተገለጹት አራት ፈረሰኞች” የሚለውን ርዕስ ሊንክ ለዘመዶቿና ለምታውቃቸው ሰዎች ልካ ነበር። በዚህም የተነሳ ሰባት ጥናቶችን አግኝታለች።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ በአንዳንድ አገሮች ውስጥ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉት በቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ አማካኝነት ነው። በስካንዲኔቪያ የምትኖር አንዲት ወጣት እህት እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ላጋጠማቸው ተማሪዎች የተዘጋጀውን “በርቀት ትምህርት ስኬታማ መሆን የምችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ በማግኘቷ ምስጋናዋን ገልጻለች። እንዲህ ብላለች፦ “የትምህርት ቤት ሥራዬን በወቅቱ ማጠናቀቅ ከብዶኝ ነበር፤ ከዚያ ግን ይህ ርዕስ ወጣ። በርዕሱ ውስጥ ያሉትን ሐሳቦች ተግባራዊ ሳደርግ ሁኔታው በጣም ተሻሻለ።”

በየቀኑ ከ1,600,000 በላይ ሰዎች የ​jw.org​ን መነሻ ገጽ ይጎበኛሉ።

የግል ጥናታችንን ለማከናወንና ‘አገልግሎታችንን በተሟላ ሁኔታ ለመፈጸም’ የሚረዱን ርዕሶች በማግኘታችን ይሖዋን እናመሰግነዋለን።—2 ጢሞቴዎስ 4:5