በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ቻጋን እና ባለቤቱ የካተሪና

መጋቢት 1, 2024
ሩሲያ

ወንድም አሌክሳንደር ቻጋን የስምንት ዓመት እስራት ተፈረደበት

ወንድም አሌክሳንደር ቻጋን የስምንት ዓመት እስራት ተፈረደበት

የካቲት 29, 2024 በሰማረ ክልል በቶልያቲ የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሳንደር ቻጋን ጥፋተኛ ነው በማለት የስምንት ዓመት እስራት ፈረደበት። አሌክሳንደር ከፍርድ ቤት ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ በአሌክሳንደርም ሆነ ለስሙ ያላቸውን ቅንዓት ይዘው በሚቀጥሉ ሁሉ ላይ ‘ፊቱን እንዲያበራ’ እንጸልያለን።​—መዝሙር 119:135, 139

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 4, 2022

    ቤቱ ተፈተሸ

  2. መስከረም 14, 2022

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  3. መስከረም 21, 2022

    ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ

  4. መስከረም 22, 2022

    የወንጀል ምርመራ ተደረገበት፤ እንዲሁም ጣቢያ አደረ

  5. መስከረም 23, 2022

    ከጣቢያ ተለቆ የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6. ነሐሴ 23, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  7. የካቲት 29, 2024

    ጥፋተኛ ነው ተብሎ የስምንት ዓመት እስራት ተፈረደበት

a ወንድም ቻጋን ይህን ሐሳብ የሰጠው ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ነው።