በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም አራም ዳኒዬልያን፣ ወንድም ዴኒስ ኩዝያኒን፣ ወንድም ሰርጌ ፖሎሴንኮ እና ወንድም ኒኮላይ ቫሲሊዬቭ

ታኅሣሥ 14, 2023 | የታደሰው፦ ጥር 30, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | “ቁልፉ በይሖዋ መታመን ነው”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | “ቁልፉ በይሖዋ መታመን ነው”

ጥር 25, 2024በሳማራ የሚገኘው የሳማርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አራም ዳኒዬልያን፣ ወንድም ዴኒስ ኩዝያኒን፣ ወንድም ሰርጌ ፖሎሴንኮ እና ወንድም ኒኮላይ ቫሲሊዬቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። እያንዳንዳቸው የሰባት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ከፍርድ ቤት ወዲያውኑ ወደ ወህኒ ተወስደዋል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ በእምነታቸው ምክንያት ስደት እየደረሰባቸው ያሉትን ሁሉ ማጽናናቱን በመቀጠል ‘መልካም የሆነውን ነገር እንዲያደርጉና እንዲናገሩ እንደሚያጸናቸው’ ሙሉ እምነት አለን።—2 ተሰሎንቄ 2:16, 17

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 14, 2021

    በዴኒስ፣ በኒኮላይ እና በሰርጌ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ

  2. ታኅሣሥ 15, 2021

    የዴኒስ፣ የኒኮላይ እና የሰርጌ ቤት ተፈተሸ። በቁጥጥር ሥር ውለው ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ተወሰዱ

  3. ታኅሣሥ 16, 2021

    ዴኒስ፣ ኒኮላይ እና ሰርጌ ወደ ማረፊያ ቤት ተዛወሩ

  4. ጥር 6, 2022

    በአራም ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ። አየር መንገድ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ

  5. ጥር 7, 2022

    አራም ማረፊያ ቤት ገባ

  6. ታኅሣሥ 12-14, 2022

    አራቱም ወንድሞች ከማረፊያ ቤት ተለቀው የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው

  7. ሰኔ 16, 2023

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ