በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቫዲም ፍዮዶሮቭ

መጋቢት 22, 2023 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 28, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ይሖዋ የሚጠብቅብኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ቆርጫለሁ”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ይሖዋ የሚጠብቅብኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ቆርጫለሁ”

ሚያዝያ 28, 2023 በቼልያቢንስክ ክልል የሚገኘው የአሻ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ቫዲም ፍዮዶሮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የስድስት ዓመት የገደብ እስራትም ፈርዶበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

እንደ ቫዲም ሁሉ እኛም፣ ይሖዋ እሱን ተስፋ የሚያደርጉትንና ‘መንገዱን የሚከተሉትን’ እንደሚባርካቸውና እንደሚያበረታቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 37:34

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 11, 2021

    የደህንነት ኃይሎች የቫዲምን እና የልጁን የአንድሬን ቤት በረበሩ

  2. ሚያዝያ 29, 2022

    ቫዲም የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  3. ታኅሣሥ 1, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ