በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ፓቬል ሲዶሬንኮ

ነሐሴ 25, 2023 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 4, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ከይሖዋ ጋር ካለኝ ወዳጅነት የበለጠ ደስታ የሚሰጠኝ ነገር የለም”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ከይሖዋ ጋር ካለኝ ወዳጅነት የበለጠ ደስታ የሚሰጠኝ ነገር የለም”

ሚያዝያ 3, 2024 በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የጎርያቼክልዩቼቭስኮይ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ፓቬል ሲዶሬንኮ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል፤ የሦስት ዓመት የገደብ እስራትም በይኖበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

እንደ ፓቬል ሁሉ እኛም “የሕይወትን መንገድ” ተከትለን ለመኖር የምናደርገው ጥረት ደስታ እንደሚያስገኝልን ስናስብ ልባችን በሐሴት ይሞላል።—መዝሙር 16:11

የክሱ ሂደት

  1. ጥር 26, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተበት

  2. ጥር 28, 2022

    ቤቱ ተፈተሸ እንዲሁም ምርመራ ከተደረገበት በኋላ የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  3. መጋቢት 22, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ