በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ ወንድም ሰርጌ ጎቦዜቭ፤ በስተ ቀኝ፦ ወንድም ሚካይል ፖታፖቭ እና ባለቤቱ ታማራ

ግንቦት 3, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 26, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | ጸሎት ብርታት ሰጥቷቸዋል

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | ጸሎት ብርታት ሰጥቷቸዋል

መጋቢት 25, 2024 በኡድሙርቲያን ሩፑብሊክ የሚገኘው የቮትኪንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ ጎቦዜቭ እና በወንድም ሚካይል ፖታፖቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሰርጌ 450,000 ሩብል (4,855 የአሜሪካ ዶላር)፣ ሚካይል ደግሞ 400,000 ሩብል (4,316 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ እንዲከፍሉ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

የክሱ ሂደት

  1. ጥር 20, 2021

    ሰርጌ እና ሚካይል የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አደራጅተዋል በሚል የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  2. ጥር 21, 2021

    የሰርጌ አፓርታማ ተፈተሸ። ባለሥልጣናቱ የሰርጌን መንጃ ፈቃድ፣ የመኪና ሰነዶች፣ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፣ የፎቶ አልበም እና የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ጨምሮ የተለያዩ የግል ንብረቶቹን ወረሱበት። ባለሥልጣናቱ ሚካይልን በቁጥጥር ሥር በማዋል ቤቱን ፈተሹ

  3. ጥር 22, 2021

    ሰርጌ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ። ሚካይል ወደ ማረፊያ ቤት ተወሰደ

  4. ግንቦት 18, 2021

    ሰርጌ ከቁም እስር ተፈታ፤ ሆኖም የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  5. ግንቦት 19, 2021

    ሚካይል ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ ሆኖም የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6. ጥቅምት 7, 2021

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ሰርጌና ሚካይል በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና በጸሎት አማካኝነት እምነታቸውን ለማጠናከር ጥረት ሲያደርጉ ይሖዋ እነሱን መደገፉን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—ቆላስይስ 2:6, 7