በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ታትያና ቦንዳሬንኮ፣ እህት ታትያና ስቮቦዳ እና ዬሌና ኔስቴሮቫ

ሐምሌ 10, 2023
ሩሲያ

በኮምሶሞልስክ ና አሙሪ ሦስት እህቶች ተፈረደባቸው

በኮምሶሞልስክ ና አሙሪ ሦስት እህቶች ተፈረደባቸው

መጋቢት 23, 2023 በኮምሶሞልስክ ና አሙሪ የሚገኘው የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ቦንዳሬንኮ፣ እህት ዬሌና ኔስቴሮቫ እና እህት ታትያና ስቮቦዳ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ውሳኔ አስተላለፈ። እያንዳንዳቸው የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ፣ መከራን ተቋቁመው ታማኝነታቸውን የጠበቁትን እህቶቻችንን እንዲባርካቸውና እንዲያበረታቸው እንጸልያለን።—ሩት 2:12

የክሱ ሂደት

  1. መስከረም 21, 2021

    ታትያና ስቮቦዳ የክስ ፋይል ተከፈተባት

  2. ጥቅምት 18, 2021

    ታትያና ቦንዳሬንኮ እና ዬሌና ኔስቴሮቫ በክስ ፋይሉ ውስጥ ተካተቱ

  3. ጥቅምት 20, 2021

    ቤታቸው ተፈተሸ

  4. ነሐሴ 28, 2022

    ክስ ተመሠረተባቸው

  5. ታኅሣሥ 28, 2022

    የወንጀል ክሶቹ በፍርድ ቤት መታየት ጀመሩ

  6. መጋቢት 23, 2023

    ጥፋተኞች ናቸው የሚል ብያኔ ተሰጠ፤ እንዲሁም እያንዳንዳቸው የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደባቸው