በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 29, 2021
ሞዛምቢክ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በንዩንግዌ ቋንቋ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በንዩንግዌ ቋንቋ ወጣ

ሰኔ 27, 2021 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በንዩንግዌ ቋንቋ ወጣ። የሞዛምቢክ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም አዳኦ ኮስታ መጽሐፍ ቅዱሱ በዲጂታል ፎርማት መውጣቱን አስቀድሞ በተቀረጸ ንግግር አማካኝነት አብስሯል። ፕሮግራሙ ከ2,600 ለሚበልጡ አስፋፊዎች ተላልፏል። በተጨማሪም በአንድ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲሁም በተለያዩ የአገሪቱ የሬዲዮ ጣቢያዎች ፕሮግራሙ ተላልፏል።

አጭር መረጃ

  • ንዩንግዌ በዋነኝነት የሚነገረው በሰሜናዊ ምዕራብ ሞዛምቢክ በሚገኘው በቴቴ ግዛት ነው

  • 400,000 ያህል ሰዎች የንዩንግዌ ቋንቋን እንደሚናገሩ ይገመታል

  • በሥራው የተካፈሉት 6 ተርጓሚዎች ሥራውን ለማጠናቀቅ 2 ዓመት ፈጅቶባቸዋል

ወንድም ኮስታ እንዲህ ብሏል፦ “ለበርካታ ዓመታት በንዩንግዌ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ አልነበረም። በመሆኑም የንዩንግዌ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች የሚጠቀሙት የቺቼዋ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር። ሆኖም ወንድሞች ብዙዎቹን የቺቼዋ ቃላትና አገላለጾች በትክክል ስለማይረዷቸው ይህ ቀላል አልነበረም።”

መጽሐፍ ቅዱሱ ከመውጣቱ በፊት አንድ የትርጉም ቡድኑ አባል እንዲህ ብሎ ነበር፦ “አስፋፊዎች ይህን ትርጉም ሲያገኙ በደስታ መፈንጠዛቸው አይቀርም። ሕልም ነው የሚሆንባቸው! ተአምር ይሆንባቸዋል! ይሖዋን በጣም እንደሚያመሰግኑት ጥያቄ የለውም።”

ይህ ትርጉም ቅን ልብ ያላቸው ብዙ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት እንዲጠቀሙ ይረዳቸው ዘንድ እንጸልያለን።—ራእይ 22:17