በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Chris McGrath/Getty Images

ጦርነት—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

ጦርነት—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

 ዓለማችን በጦርነት እየታመሰች ነው፤ በዚህም የተነሳ ብዙዎች ለከፍተኛ ሥቃይና መከራ ተዳርገዋል። እስቲ የሚከተሉትን ሪፖርቶች ተመልከት፦

  •   “አዲስ የወጡት አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከጦርነት ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር፣ ባለፉት 28 ዓመታት ውስጥ ከተመዘገቡት ቁጥሮች ሁሉ ከፍተኛው ነው፤ ለዚህም እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሰው በኢትዮጵያና በዩክሬን የተቀሰቀሰው ጦርነት ነው።”—የኦስሎ የሰላም ምርምር ተቋም፣ ሰኔ 7, 2023

  •   “የዩክሬን ጦርነት በ2022 ከተፋፋሙት ጦርነቶች መካከል አንዱ ብቻ ነው። በጥቅሉ ሲታይ ባለፈው ዓመት ውስጥ ፖለቲካዊ ግጭቶች በዓለም ዙሪያ 27 በመቶ ጨምረዋል፤ በግምት 1.7 ቢሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች በዚህ የተነሳ ለችግር ተዳርገዋል።”—ጦርነቶች የሚካሄዱባቸው ቦታዎችና ተያያዥ ክስተቶች ጥናት ፕሮጀክት (ACLED)፣ የካቲት 8, 2023

 መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይሰጣል። “የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል” በማለት ይናገራል። (ዳንኤል 2:44) አምላክ በዚህ መንግሥት ወይም አገዛዝ አማካኝነት “ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።”—መዝሙር 46:9