በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንጉሥ ዳዊት በእርግጥ ምድር ላይ የኖረ ሰው መሆኑን የሚያሳይ የአርኪኦሎጂ ማስረጃ

ንጉሥ ዳዊት በእርግጥ ምድር ላይ የኖረ ሰው መሆኑን የሚያሳይ የአርኪኦሎጂ ማስረጃ

 መጽሐፍ ቅዱስ ንጉሥ ዳዊት በ11ኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. በእስራኤል የኖረ ሰው እንደሆነና ዘሮቹ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት እንደነገሡ ይናገራል። ሆኖም አንዳንድ ምሁራን የዳዊት ታሪክ እውነተኛ እንዳልሆነ ከዚህ ይልቅ ከጊዜ በኋላ የተፈጠረ የብሔሩ አፈ ታሪክ እንደሆነ ይከራከራሉ። ንጉሥ ዳዊት በእርግጥ በምድር ላይ ኖሯል?

 በ1993 አቭራአም ቢራን የተባሉ የአርኪኦሎጂ ባለሙያና የሥራ ባልደረቦቻቸው በሰሜናዊ እስራኤል በሚገኘው በቴል ዳን “የዳዊት ቤት” የሚል ጽሑፍ የተቀረጸበት ድንጋይ አገኙ። በጥንታዊ ሴማዊ ፊደል የተጻፈው ይህ ጽሑፍ የተቀረጸው በዘጠነኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ነው። ድንጋዩ አራማውያን በእስራኤላውያን ላይ ለተቀዳጇቸው ድሎች መታሰቢያ እንዲሆን ያቆሙት ሐውልት ክፍል ሳይሆን አይቀርም።

 በባይብል ሂስትሪ ዴይሊ ላይ የወጣ አንድ ርዕስ እንዲህ ይላል፦ “‘የዳዊት ቤት’ የሚለውን የተቀረጸ ጽሑፍ አስመልክቶ የተለያየ አመለካከት ያላቸው ሰዎች አሉ። . . . ያም ሆኖ አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራንና የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች በቴል ዳን የተገኘው ድንጋይ የመጽሐፍ ቅዱሱ ንጉሥ ዳዊት በእርግጥ በምድር ላይ የኖረ ሰው እንደሆነ የሚያሳይ የመጀመሪያው ጠንካራ ማስረጃ እንደሆነ ይቀበላሉ፤ በዚህም ምክንያት ይህ ድንጋይ በቢብሊካል አርኪኦሎጂ ሪቪው ላይ ከወጡት ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የአርኪኦሎጂ ግኝቶች አንዱ ሆኗል።”