በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

Francesco Carta fotografo/Moment via Getty Images

እየተባባሰ የመጣው የብቸኝነት ወረርሽኝ—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

እየተባባሰ የመጣው የብቸኝነት ወረርሽኝ—⁠መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በቅርቡ የወጣ አንድ ዓለም አቀፋዊ ሪፖርት a እንደሚገልጸው ከአራት ሰዎች አንዱ ብቸኝነት ይሰማዋል።

  •   “ብቸኝነት በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩና በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል።”​—ቺዶ ምፔምባ፣ የዓለም የጤና ድርጅት የማኅበራዊ ግንኙነት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር

 ብዙዎች ከሚያስቡት በተለየ መልኩ ብቸኝነት የሚያጠቃው በዕድሜ የገፉ ወይም ብቻቸውን የሚኖሩ ሰዎችን ብቻ አይደለም፤ ወጣት፣ ጤናማ፣ ስኬታማና ባለትዳር የሆኑ ሰዎችም በብቸኝነት ሊጠቁ ይችላሉ። ብቸኝነት የአንድን ሰው አካላዊና ስሜታዊ ጤንነት በእጅጉ ሊጎዳ ይችላል።

  •   የአሜሪካ የማኅበረሰብ ጤና ባለሥልጣን የሆኑት ዶክተር ቪቬክ ሙርቲ “ብቸኝነት ከተራ ድብታ ያለፈ ነገር ነው” ብለዋል። አክለውም እንዲህ ብለዋል፦ “ብቸኝነት ያለው ለሞት የመዳረግ አቅም በቀን 15 ሲጋራ ከማጨስ ጋር ተመጣጣኝ ነው።”

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ፈጣሪያችን ብቸኛ እንድንሆን አይፈልግም። ከጅምሩ አንስቶ የአምላክ ዓላማ ሰዎች ጥሩና አርኪ የሆነ ወዳጅነት እንዲመሠርቱ ነው።

  •   የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “አምላክ ‘ሰውየው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም’ . . . አለ።”​—ዘፍጥረት 2:18

 አምላክ ከእሱ ጋር ወዳጅነት እንድንመሠርት ይፈልጋል። ወደ እሱ ለመቅረብ ጥረት ካደረግን እሱም ወደ እኛ እንደሚቀርብ ቃል ገብቶልናል።​—ያዕቆብ 4:8

  •   የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ነውና።”​—ማቴዎስ 5:3

 አምላክ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብረን ሆነን እንድናመልከው ይፈልጋል። እንዲህ ማድረጋችን ደስተኛ እንድንሆን ይረዳናል።

  •   የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ . . . መሰብሰባችንን ቸል አንበል፤ ከዚህ ይልቅ እርስ በርስ እንበረታታ።”​—ዕብራውያን 10:24, 25

 ብቸኝነትን ማሸነፍ አስፈላጊ ስለሆነበት ምክንያት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ብቸኝነት የመገናኛ ዘዴዎች በሞሉበት ዓለም” የሚለውን ርዕስ አንብብ።