በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 9

ይሖዋ ንጉሣችን ነው!

ይሖዋ ንጉሣችን ነው!

(መዝሙር 97:1)

  1. 1. ያህን በደስታ አወድሱት፤

    ያምላክን ጽድቅ ያውጃሉ ሰማያት።

    በደስታ እንዘምር፤ ከፍ እና’ርገው ስሙን፤

    እናሳውቅ ታላቅ ሥራውን።

    (አዝማች)

    ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤

    ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!

    ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤

    ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!

  2. 2. ዓለም ይወቀው የሱን ግርማ፤

    ማዳኑን ንገሩ፤ ሁሉም ሰው ይስማ።

    ይሖዋ ንጉሥ ነው፤ ይገባል ሊከበር።

    በዙፋኑ ፊት እንንበርከክ።

    (አዝማች)

    ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤

    ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!

    ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤

    ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!

  3. 3. ጻድቅ መንግሥቱ ተቋቁሟል፤

    ልጁንም ሾሞታል፤

    ሥልጣን ሰጥቶታል።

    ክብር የሚገባው ይሖዋ ብቻ ነው፤

    አማልክት ይስገዱለት አፍረው።

    (አዝማች)

    ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤

    ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!

    ሰማይም ይደሰት፤ ምድርም እልል ትበል፤

    ይሖዋ ንጉሣችን ሆኗል!

(በተጨማሪም 1 ዜና 16:9⁠ን፣ መዝ. 68:20⁠ን እና 97:6, 7⁠ን ተመልከት።)