በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 85

አንዳችን ሌላውን መቀበል

አንዳችን ሌላውን መቀበል

(ሮም 15:7)

  1. 1. ዛሬ ከኛ ጋር የተገኛችሁ፣

    ደስ ብሎናል ስለመጣችሁ።

    ቃሉን ’ንድንሰማ አምላክ ጋብዞናል፤

    ጥሪውን አክብረን ቤቱ ተገኝተናል።

  2. 2. ይሖዋ ሰጠን ውድ ወንድሞችን፤

    ሁሌም በደስታ ’ሚቀበሉን።

    እናክብራቸው እንዲህ ያሉትን፤

    እኛም እንቀበል እንግዶቻችንን።

  3. 3. ቅኖች እውነትን መጥተው ’ንዲማሩ፣

    ለሰው ሁሉ ተከፍቷል በሩ።

    ልባዊ ፍቅር እናሳያቸው፤

    በ’የሱስ በኩል ነው አምላክ የሳባቸው።

(በተጨማሪም ዮሐ. 6:44⁠ን፣ ፊልጵ. 2:29⁠ን እና ራእይ 22:17⁠ን ተመልከት።)