በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 81

የአቅኚ ሕይወት

የአቅኚ ሕይወት

(መክብብ 11:6)

  1. 1. ጠዋት በማለዳ፣ ፀሐይዋ ሳትወጣ፣

    ከእንቅልፍ ተነስተን፣

    ጸልየን እንሰማራለን።

    በፈገግታ ለሰው ሰላምታ ’ንሰጣለን።

    ቢቆሙም፣ ቢሄዱም፣

    እኛ ግን ሁልጊዜ እዚያው ነን።

    (አዝማች)

    ይህንን ሕይወት ነው፣

    ወደን የመረጥነው፤

    ለይሖዋ ነው የምንኖረው።

    በፀሐይ፣ በዝናብ፣

    ስናውጅ ምሥራች፣

    ላምላክ ያለን ፍቅር ይታያል ለሰዎች።

  2. 2. ቀኑ ሲገባደድ፣ ፀሐይዋ ስትጠልቅ፣

    ደክሞንም ብርቱ ነን፤

    በደስታ እንጸልያለን።

    ወደናል ለመስጠት ላምላክ ምርጣችንን።

    ይሖዋ ይመስገን፣

    በረከቱ ስላልተለየን።

    (አዝማች)

    ይህንን ሕይወት ነው፣

    ወደን የመረጥነው፤

    ለይሖዋ ነው የምንኖረው።

    በፀሐይ፣ በዝናብ፣

    ስናውጅ ምሥራች፣

    ላምላክ ያለን ፍቅር ይታያል ለሰዎች።

(በተጨማሪም ኢያሱ 24:15⁠ን፣ መዝ. 92:2⁠ን እና ሮም 14:8⁠ን ተመልከት።)