በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 71

የይሖዋ ሠራዊት ነን!

የይሖዋ ሠራዊት ነን!

(ኤፌሶን 6:11-14)

  1. 1. የአምላክ ሠራዊት ነን፤

    ’የሱስ ’ሚመራን።

    ሰይጣን ቢቃወመንም

    ፍርሃት አይሰማንም።

    እንገፋለን ወደፊት፣

    በታማኝነት።

    አለን ጽኑ አቋም፤

    ቅንጣት አንፈራም።

    (አዝማች)

    የአምላክ ሠራዊት ነን፣

    ከ’የሱስ ጋር አንድ፤

    መግዛት መጀመሩን

    በደስታ ’ናውጅ።

  2. 2. ያምላክ አገልጋዮች ነን፤

    እንፈልጋለን

    የባዘኑ በጎችን፤

    ’ሚያለቅሱ፣ ’ሚያዝኑትን።

    እንርዳቸው ቅኖችን

    ሳንሰለች ሄደን።

    እንጋብዛቸው ሁሌ፣

    ወደ ጉባኤ።

    (አዝማች)

    የአምላክ ሠራዊት ነን፣

    ከ’የሱስ ጋር አንድ፤

    መግዛት መጀመሩን

    በደስታ ’ናውጅ።

  3. 3. የአምላክ ሠራዊት ነን፤

    እንዘምታለን

    ትጥቃችንን አሟልተን፣

    ቦታችንን ይዘን።

    ቆራጥ አቋም ይኑረን፤

    ጥንቁቆች እንሁን።

    በአስቸጋሪም ወቅት፣

    እንጽና በ’ውነት።

    (አዝማች)

    የአምላክ ሠራዊት ነን፣

    ከ’የሱስ ጋር አንድ፤

    መግዛት መጀመሩን

    በደስታ ’ናውጅ።

(በተጨማሪም ፊልጵ. 1:7⁠ን እና ፊልሞና 2⁠ን ተመልከት።)