በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 59

ያህን አብረን እናወድስ

ያህን አብረን እናወድስ

(መዝሙር 146:2)

  1. 1. ያህን አብረን

    እናወድስ!

    ሰጥቶናል ሕይወትና እስትንፋስ።

    ስሙን እንባርክ፣

    ሌትና ቀን።

    እንናገር ሁሉን ቻይ መሆኑን፤

    እንዘምር፣ እናሳውቅ ስሙን።

  2. 2. ያህን አብረን

    እናወድስ!

    ጸሎት ሰምቶ ይሰጣልና መልስ።

    ደካማውን

    ይደግፋል፤

    ለትሑታን መንፈሱን ይሰጣል።

    ’ናውጃለን ያለውን ታላቅ ኃይል።

  3. 3. ያህን አብረን

    ’ናወድሰው!

    ያጽናናናል፣ የፍትሕ አምላክ ነው።

    ልባችንን

    ይጠግናል፤

    በረከቱን ለሁሉም ያፈሳል።

    ኑ በደስታ እንበልለት እልል።

(በተጨማሪም መዝ. 94:18, 19⁠፤ 145:21⁠፤ 147:1⁠፤ 150:2⁠ን እና ሥራ 17:25⁠ን ተመልከት።)