በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 56

እውነትን የራስህ አድርግ

እውነትን የራስህ አድርግ

(ምሳሌ 3:1, 2)

  1. 1. የእውነት መንገድ በጣም ግሩም ሕይወት ነው፤

    መምረጥ ግን የራስህ ድርሻ ነው።

    ስለዚህ ስማ ይሖዋ ’ምላክ ሲመክርህ፤

    በሱ ላይ እምነት ይኑርህ።

    (አዝማች)

    በ’ውነት መንገድ ሂድ፤

    እውነት ይሁን የራስህ።

    ያኔ ይሖዋ

    ይባርክሃል፤

    ደስታህም ይጨምራል።

  2. 2. ይሖዋንና መንግሥቱን ለማስቀደም

    ጊዜና ጥረት ቢጠይቅም፣

    ባዲሱ ዓለም ደስታና አርኪ ሕይወት

    ይኖረናል ለዘላለም።

    (አዝማች)

    በ’ውነት መንገድ ሂድ፤

    እውነት ይሁን የራስህ።

    ያኔ ይሖዋ

    ይባርክሃል፤

    ደስታህም ይጨምራል።

  3. 3. በይሖዋ ዘንድ ሁላችንም ልጆች ነን፤

    የሱን መመሪያ እንሻለን።

    ከይሖዋ ጋር ሁሌም አብረን ከሄድን

    በረከቱን እናጭዳለን።

    (አዝማች)

    በ’ውነት መንገድ ሂድ፤

    እውነት ይሁን የራስህ።

    ያኔ ይሖዋ

    ይባርክሃል፤

    ደስታህም ይጨምራል።

(በተጨማሪም መዝ. 26:3⁠ን፣ ምሳሌ 8:35⁠፤ 15:31⁠ን እና ዮሐ. 8:31, 32⁠ን ተመልከት።)