በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 54

“መንገዱ ይህ ነው”

“መንገዱ ይህ ነው”

(ኢሳይያስ 30:20, 21)

  1. 1. የሰላም መንገድ ነው፤

    አንተም አውቀኸዋል።

    የጥንቱ መንገድ ነው፤

    ተገንዝበኸዋል።

    ’የሱስ ያስተማረህ፣

    በሱ እንድትሄድ።

    ባምላክ ቃል ውስጥ ያለ፣

    ሰላም ’ሚያስገኝ መንገድ።

    (አዝማች)

    ይህ የሕይወት መንገድ፣ ነው የሕይወት።

    ዞር አትበል፤ ላፍታም ፈቀቅ አትበል!

    አምላክ ብሏል፦ ‘ይህ ነው መንገዱ፤

    ተው አትዙር፤ ይሄ ነው መንገዱ።’

  2. 2. የፍቅር መንገድ ነው፤

    የለም የተሻለ።

    ጆሮህ ሰምቷል ድምፁን

    ‘በዚህ ሂድ’ እንዳለ።

    ፍቅሩ እጅግ መልካም፣

    እውነተኛ፣ ፍጹም።

    ይሄ መንገድ ይሁን

    መላ ሕይወታችን።

    (አዝማች)

    ይህ የሕይወት መንገድ፣ ነው የሕይወት።

    ዞር አትበል፤ ላፍታም ፈቀቅ አትበል!

    አምላክ ብሏል፦ ‘ይህ ነው መንገዱ፤

    ተው አትዙር፤ ይሄ ነው መንገዱ።’

  3. 3. የሕይወት መንገድ ነው፤

    አትይ ወደ ኋላ።

    አምላካችን ብሏል፦

    የለም ከዚህ ሌላ፤

    የተሻለ ፍቅር፣

    የተሻለ ሰላም።

    ይሖዋ ይመስገን

    መንገዱን አሳየን።

    (አዝማች)

    ይህ የሕይወት መንገድ፣ ነው የሕይወት።

    ዞር አትበል፤ ላፍታም ፈቀቅ አትበል!

    አምላክ ብሏል፦ ‘ይህ ነው መንገዱ፤

    ተው አትዙር፤ ይሄ ነው መንገዱ።’

(በተጨማሪም መዝ. 32:8⁠፤ 139:24⁠ን እና ምሳሌ 6:23⁠ን ተመልከት።)