በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 51

ራሳችንን ለአምላክ ወስነናል!

ራሳችንን ለአምላክ ወስነናል!

(ማቴዎስ 16:24)

  1. 1. የሰማዩ አባት ወደ ልጁ ሳበን፤

    የ’የሱስ ተከታዮች ሆንን።

    ከአምላክ ታላቅ ዙፋን፣

    ፈንጥቋል የ’ውነት ብርሃን።

    እምነታችን ጠንክሯል፤

    ራሳችንን ክደናል።

    (አዝማች)

    ወደን ላምላክ ራሳችንን ወስነናል፤

    የሱ መሆናችን ደስ ይለናል።

  2. 2. ዘላለም አምላካችንን ለማገልገል፣

    በጸሎት ለሱ ቃል ገብተናል።

    ወደር የለውም ደስታው፣

    ውስጣዊ እርካታ ’ለው፣

    ለቅኖች ቃሉን መስበክ፣

    በአምላክ ስም መታወቅ።

    (አዝማች)

    ወደን ላምላክ ራሳችንን ወስነናል፤

    የሱ መሆናችን ደስ ይለናል።

(በተጨማሪም መዝ. 43:3⁠፤ 107:22⁠ን እና ዮሐ. 6:44⁠ን ተመልከት።)