በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 37

ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል

ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል

(ማቴዎስ 22:37)

  1. 1. ይሖዋ ሆይ፣ ሉዓላዊው፣

    አንተን ልውደድህ፣ ላገልግልህ።

    ላንተ ልደር በሙሉ ነፍስ፤

    በየ’ለቱ አንተን ላወድስ።

    ሕግጋትህን አከብራለሁ፤

    ት’ዛዛትህን ’ወዳለሁ።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ሆይ፣ ይገባሃል፤

    በሙሉ ነፍስ አንተን ላገልግል።

  2. 2. ፀሐይ፣ ጨረቃና ምድር፣

    ይናገራሉ ያንተን ክብር።

    እኔም እመሠክራለሁ፤

    ቅዱስ ስምህን አውጃለሁ።

    ላገለግልህ ወስኛለሁ፣

    ሕይወቴን ሰጥቼሃለሁ።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ሆይ፣ ይገባሃል፤

    በሙሉ ነፍስ አንተን ላገልግል።

(በተጨማሪም ዘዳ. 6:15⁠ን፣ መዝ. 40:8፣ 113:1-3⁠ን፣ መክ. 5:4⁠ን እና ዮሐ. 4:34⁠ን ተመልከት።)