በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 35

‘ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ እወቁ’

‘ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ እወቁ’

(ፊልጵስዩስ 1:10)

  1. 1. ለመለየት እውነት የሆነውን፣

    ለመለየት መልካሙን፣

    ለማወቅ ይበልጥ አስፈላጊውን፣

    ይገባናል ማስተዋል!

    (አዝማች)

    አምላካችን ይደሰታል

    ክፉን ጠልተን ጥሩን ስንወድ፤

    መቅደም ያለበትን

    ስናስቀድም

    በረከቱን እናገኛለን!

  2. 2. የመንግሥቱን ምሥራች ከመስበክ፣

    ቅኖችን ከመፈለግ፣

    ወዳምላክ ከመምራት የተሻለ፣

    ሌላ ምን ሥራ አለ?

    (አዝማች)

    አምላካችን ይደሰታል

    ክፉን ጠልተን ጥሩን ስንወድ፤

    መቅደም ያለበትን

    ስናስቀድም

    በረከቱን እናገኛለን!

  3. 3. አስፈላጊ ነገር ላይ ማተኮር

    እርካታ ይሰጠናል፤

    ውስጣዊ ሰላም እናገኛለን፤

    ልባችን ይረጋጋል።

    (አዝማች)

    አምላካችን ይደሰታል

    ክፉን ጠልተን ጥሩን ስንወድ፤

    መቅደም ያለበትን

    ስናስቀድም

    በረከቱን እናገኛለን!

(በተጨማሪም መዝ. 97:10⁠ን፣ ዮሐ. 21:15-17⁠ን እና ፊልጵ. 4:7⁠ን ተመልከት።)