በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 29

እንደ ስማችን መኖር

እንደ ስማችን መኖር

(ኢሳይያስ 43:10-12)

  1. 1. ልዑል ይሖዋ፣ ዘላለማዊ ነህ፤

    በፍቅርህ፣ በኃይልህ አቻ የለህ።

    አንተ ነህ ምንጩ የጥበብ፣ የእውነት፤

    ሉዓላዊ፣ ሁሉን ቻይ ጌታ ነህ።

    በጣም ያስደስታል አንተን ማገልገል፤

    እውነትንም ለሰዎች መናገር።

    (አዝማች)

    ምሥክሮችህ መሆን ታላቅ መብት ነው፤

    እርዳን እንደ ስማችን ለመኖር!

  2. 2. በአገልግሎት አብረን ስንካፈል

    አንድነታችን ይጠናከራል።

    ስለ ክብርህ ለሰዎች ስንናገር፣

    አንተን ስናወድስ ደስ ይለናል።

    አባታችን ሆይ፣ በስምህ ተጠራን፤

    ዝናህን ለማወጅ መብት አገኘን።

    (አዝማች)

    ምሥክሮችህ መሆን ታላቅ መብት ነው፤

    እርዳን እንደ ስማችን ለመኖር!

(በተጨማሪም ዘዳ. 32:4⁠ን፣ መዝ. 43:3⁠ን እና ዳን. 2:20, 21⁠ን ተመልከት።)