በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 18

ለቤዛው አመስጋኝ መሆን

ለቤዛው አመስጋኝ መሆን

(ሉቃስ 22:20)

  1. 1. ይሖዋ ሆይ፣

    ባንተ ፊት መቆም ችለናል፤

    ከሁሉ የላቀ ፍቅር

    ስላሳየኸን።

    ልጅህን ላክህልን

    እንዲሆነን ቤዛ፤

    ሊኖር አይችልም

    ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ።

    (አዝማች)

    እኛን ሊያድን እሱ ሞተ፤

    ክቡር ደሙን ለኛ ሰጠ።

    ለዘላለም

    ልባዊ ምስጋና ይድረስ ላንተ።

  2. 2. ኢየሱስ ቤዛችን የሆነው

    ፈቅዶ ነው፤

    ሕይወቱን እንዲሰጠን

    ፍቅር አነሳሳው።

    ማንም አልነበረም

    ከሞት ’ሚታደገን፤

    ልጅህ ደረሰልን

    አሁን ሕይወት አገኘን።

    (አዝማች)

    እኛን ሊያድን እሱ ሞተ፤

    ክቡር ደሙን ለኛ ሰጠ።

    ለዘላለም

    ልባዊ ምስጋና ይድረስ ላንተ።

(በተጨማሪም ዕብ. 9:13, 14⁠ን እና 1 ጴጥ. 1:18, 19⁠ን ተመልከት።)