በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 145

አምላክ የሰጠው የገነት ተስፋ

አምላክ የሰጠው የገነት ተስፋ

(ሉቃስ 23:43)

  1. 1. በክርስቶስ ሺህ ዓመት ግዛት፣

    ትሆናለች ምድር ገነት።

    ኃጢያት፣ በደል ይደመሰሳል፤

    ሥቃይ፣ ሞትም ይወገዳል።

    (አዝማች)

    ምድርን ገነት ያደርጋታል፤

    በእምነት ዓይን ይታየናል።

    ተስፋው በቅርብ ይፈጸማል፤

    የገባው ቃል ይታመናል።

  2. 2. ሙታን በቅርብ ተስፋ አላቸው፤

    ይነሳሉ፣ ዓላማው ነው።

    ‘በገነት ውስጥ ትኖራለህ’ ሲል

    የአምላክ ልጅ ተስፋ ሰጥቷል።

    (አዝማች)

    ምድርን ገነት ያደርጋታል፤

    በእምነት ዓይን ይታየናል።

    ተስፋው በቅርብ ይፈጸማል፤

    የገባው ቃል ይታመናል።

  3. 3. የአምላክ ልጅ ተስፋ ሰጥቶናል፤

    የምድራችን ንጉሥ ሆኗል።

    ምስጋናችን ላምላክ ይድረሰው፤

    በየ’ለቱ ’ናወድሰው።

    (አዝማች)

    ምድርን ገነት ያደርጋታል፤

    በእምነት ዓይን ይታየናል።

    ተስፋው በቅርብ ይፈጸማል፤

    የገባው ቃል ይታመናል።

(በተጨማሪም ማቴ. 5:5⁠፤ 6:10⁠ን እና ዮሐ. 5:28, 29⁠ን ተመልከት።)