በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 140

መጨረሻ የሌለው ሕይወት

መጨረሻ የሌለው ሕይወት

(ዮሐንስ 3:16)

  1. 1. ይታይህ ባዲስ ዓለም፤

    ሁሉም ሲኖር ዘላለም።

    ሐዘን፣ ሥቃይ ተረስቶ፤

    ሰላም፣ ደስታ ሰፍኖ።

    (አዝማች)

    ከልብ እንዘምር

    ለዚህ ቀን ላበቃን።

    መጨረሻ የሌለው፣

    ሕይወት ልናገኝ ነው!

  2. 2. እርጅና ይወገዳል፤

    ሰውም ፍጹም ይሆናል።

    ነፃ ስንሆን ከችግር፣

    አይኖር ለቅሶ፣ ሽብር።

    (አዝማች)

    ከልብ እንዘምር

    ለዚህ ቀን ላበቃን።

    መጨረሻ የሌለው፣

    ሕይወት ልናገኝ ነው!

  3. 3. ሁላችን ገነት ገብተን፣

    በደስታ እ’ኖራለን።

    ለዘላለም ይሖዋን

    ’ናመሰግናለን።

    (አዝማች)

    ከልብ እንዘምር

    ለዚህ ቀን ላበቃን።

    መጨረሻ የሌለው፣

    ሕይወት ልናገኝ ነው!

(በተጨማሪም ኢዮብ 33:25⁠ን፣ መዝ. 72:7⁠ን እና ራእይ 21:4⁠ን ተመልከት።)